የስራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የድሬደዋ አስተዳደር የምክር ቤት አባላትና አስፈፃሚ አካላት የእውቅና መርሀ-ግብር ተካሄደ ።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 2 ተኛ የስራ ዘመን 48 ተኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል ፤ በትናንትናው እለትም በምክር ቤቱ ለባለፍት የስራ ዘመናት የጎላ አስተዋፆ ላደረጉ የምክር ቤት አካላትና አስፈፃሚ አካላት በራስ-ሆቴል የእውቅና ፕሮግራም ተካሂዷል ።
    በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ\ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በተለይም በከተማችን ድሬዳዋ ላይ የነበረውን የፀጥታ ችግርን በጋራ በመስራት ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል የምክር ቤቱ አባላትና የአስፈፃሚ አካላት ስራዎች ማሳያ መሆኑን ተናግረው ነባሩ ምክር ቤት ባለፍት ስምንት አመት ያካበቱትን ልምድ ለቀጣዩ ምክር ቤት የማማከርና የማገዝ ስራዎች እንደሚሰሩ ገልፀዋል ።
    ላለፍት ስምንት አመት ያገለገሉ የምክር ቤት አባላት ብሎም የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ በተለይም ከተማችን ድሬዳዋ አጋጥሟት ከነበረው የፀጥታ ችግር በመውጣት ፍፁም ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማ ትሆን ዘንድ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፆ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀር በእለቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
    በፕሮግራሙ መጨረሻም ባለፍት አመታት በምክር ቤት የጎላ አስተዋፆ ለነበራቸው የምክር ቤት አባላትና አስፈፃሚ አካላት ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ የእውቅና ሽልማታቸውን ወስደዋል ።