የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

    የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት በምክር ቤቱ አዋጅ ቁጥር 1/2000 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን እነርሱም የሚከተሉት ናቸው፡-

    የጽ/ቤቱ አፈ-ጉባኤ በሚሰጠው አመራር መሰረት፡-

    1. ለምክር ቤቱና ምክር ቤቱ ለሚያቋቁማቸው ኮሚቴዎች ውስጣዊ አካላት አጠቃላይ አስተዳደራዊ ግልጋሎት ይሰጣል፣
    2. ለምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤና ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች የሚያስፈልጉትን የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ያደራጃል የዘጋጃል አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
    3. የምክር ቤቱን ቃለ-ጉባኤዎች፣ ውሳኔዎችና ሰነዶች በሚገባ ተመዝግበው እንዲቀመጡ ያደርጋል፣
    4. የምክር ቤቱ አካላትና አባላት የቤተ መፃህፍት፣ የምርምርና የመረጃ አገልግሎት ይሰጣል፣
    5. ምክር ቤቱ የሚያወጣቸው መጽሄቶችና ጋዜጣዎች ህትመትና ስርጭት ይከታተላል፣
    6. ለምክር ቤቱ እንግዶች አስፈላጊውን የመስተንግዶ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፣
    7. የሀብት ባለቤት ይሆናል፣ በስሙ ይከሳል ይከሰሳል፣
    8. የምክር ቤቱ አካላትና አባሎች ስራቸውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባሮችን ያከናውናል፣

     

    የምክር ቤቱ ራዕይ

    በ2014 በተሟላ ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎት አሰጣጥ በሀገሪቱ ውስጥ ተምሳሌት የሆኑ የምክር ቤታዊ አገልግሎት ሰጭ ጽ/ቤት ሆኖ ማየት፤

     

    የምክር ቤቱ ተልዕኮ

    የምክር ቤት ጽ/ቤት የምክር ቤቱ  አባላትና አካላት የህግ አወጣጥ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የውክልና ስራ በመተግበር መንገድ እንዲከናወኑ ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎት በተሟላ መልኩ መስጠት፡፡

     

     

    እሴቶች

    • ለህገ መንግስቱና ለመራጩ ህዝብ ተገዢ መሆን፣
    • የአሰራር ሥርዓት ፣ግልፅነትና ቅልጥፍና፣ታማኝነትና የህዝብ አገልጋይነት ስሜት መፍጠር፣
    • ወንድማማችነትንና የጋራ መግባባትን ማስፈን፣
    • የዘር ፣የሃይማኖት፣የፆታ እና የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይደረግ ለሁሉም ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት፣
    • ግልፅነት ፣ቅንነት ፣አሳታፊነት እና የተጠያቂነትን መንፈስ መፍጠር፣

     

    ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

    3.1. የትኩረት መስኮች

    • የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ
    • የላቀ ግንዛቤ መፍጠር
    • የማህበረሰብ ተሳታፊነት

    3.2. የስትራቴጂያዊ ውጤቶች

    በእያንዳንዱ የትኩረት መስክ የሚቀረጹ ግቦች የሚያመጡትን አጠቃላይ ስኬት፣እስትራቴጂያዊ እሳቤዎች የሚያመጡትን የመጨረሻ ውጤት የሚያመለክቱና ወደ ተቋሙ ተልእኮና ራዕይ ስኬት የሚያመሩ ስትራቴጂያዊ ውጤቶችን ከዚህ እንደሚከተለው ተመልክተዋል፡፡

    የትኩረትመስክ 1፡- የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ

    ውጤት፡ተገልጋዮችንና ባለድርሻ አካላትን ያረካ ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣

    የትኩረት መስክ 2የላቀ ግንዛቤ መፍጠር

        ወጤት፡የዳበረ የተገልጋይና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ መፍጠር

    የትኩረትመስክ 3የማህበረሰብ ተሳታፊነት

     

        ወጤት፡- የጨመረ የዜጎች ፍላጎትና ተሳታፊነትን ማሳደግ ……ራእይ እና ተልእኮ