በምርቃት ስነስረአቱ የኮሌጁ ፕሬዝዳንት አቶ በላይነህ ረጋሳ ተቋሙ ከተመሰረተበት ከ1997 ዓም ጀምሮ ተማሪዎቹን በዘርፉ በተቀመጠው የጥራት ደረጃ ልክ በእውቀትና በክህሎት ጎልብተው እንዲመረቁ ከማስቻል ባለፈ ከፍሎ ለመማር ላልቻሉ ወገኖች በተለያዩ ጊዜያት ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጓ በማስተማርና በማስመረቅ ማህበራዊ ግዴታውን መወጣቱን አስረድተዋል።በቀጣይም ኮሌጁ ትምህርት አሰጣጡን ዘመናዊ ለማድረግ እየሰራ ያለውን ተግባር በማጠናከር የመማር ማስተማር ሂደቱን ወደላቀ ደረጃ የማድረስ እቅድ ለማሳካት በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አስረድተዋል።
አቶ መለስ ቢራቱ የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን በበኩላቸው አገሪቱ በየዘርፉ የሚያስፈልጋትን የተማረ የሰው ሃይል በማፍራት እረገድ አንድ አማራጭ የትምህርት ተቋም በመሆን የራሱን አስተዋፆ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።በቀጣይም የሚሰጣቸውን የትምህርትና ስልጠና ዘርፎች በማስፋት በጥራትና በብቃት ተማሪዎችን ለማፍራት በትጋት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል አቶ ሀብታሙ ገቢሳ የኮሌጁ ስራ አስኪሃጅ ተቋሙ አገልግሎቱን በማጠናከር የበለጠ ስኬታማ ስራ ለማከናወን እንደሚሰራ ገልፀዋል።ስራ አስኪሃጁ አክለውም የኮሌጁ ተማሪዎች የትብብር ስልጠና እንዲያደርጉ ፍቃደኛ ሆነው ላስተናገዱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።በዛሬው እለት የተመረቁ ተማሪዎች ሙያዊ ግዴታቸውን በመወጣት ለአገራችን እድገት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል።
በኮሌጁ በማስተርስ ዲግሪ የተመረቁትና በክብር እንግድነት ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ኮሌጁ ብቃት ያለው የተማረ የሰው ሃይል በማፍራት አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ እነወደሚገኝ ገልፀው አገራችንን ወደ ብልፅግና ማማ ለማድረስ የተጣለውን እቅድ እውን ለማድረግ በየዘርፉ ወደ ሚፈለገው የእድገት ደረጃ ለመድረስ ተመራቂ ተማሪዎች ሙያዊ ግዴታቸውን በብቃት እና በቅንነት በመወጣት የዜግነትና ሙያቸው የሚጠይቀውን ሃላፊነት እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል።
ኮሌጁ በአካውንቲንግ እና ቢዝነስ ማኔጅመንት፣ በማስተርስ ኦፍ ኤምቢኤ፣ በነርሲንግና ፈርማሲ በጥቅሉ 162 ወንድ 158 ሴት በድምሩ 320 ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ የትመህርት ዘርፍ በመጀመሪያ ዲግሪና በማስተርስ ዲግሪ ዛሬ ማስመረቁን ለማወቅ ተችሏል።


