በድሬዳዋ አስተዳደር የተጀመረው ከተማ አቀፍ የጽዳት ዘመቻ 3ኛ ሳምንት መርሀ ግብር፤ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ.ም፤ ከማለዳው 12:00 ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለፀ።
በፅዳት ዘመቻው የአስተዳደሩ መንግስታዊ ሴክተር መ/ቤቶችና የቀበሌ አስተዳደደር ፅ/ቤት ሰራተኞች፤ በ2 ቡድን ተከፍለው በከተማዋ የተመረጡ 2 ዋና ዋና መንገዶችንና የፍሳሽ መውረጃ ቦዮችን የማጽዳት፤ እንዲሁም ችግኝ የመትከል ተግባር እንደሚያከናውኑ የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
ከንቲባው አክለውም በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ከጎናችን ሆናችሁ፤ የምንወዳትን ከተማችንን ወደ ቀድሞ ንፅህናዋ እና ውበቷ ተባብረን እንመልሳት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።


