የፖሊዮ ቫይረስ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ
በዘመቻው እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን በሙሉ ከጥቅምት 12 -15 ቤት ለቤት ለመድረስ ታስቧል።
የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በዘመቻ የሚሰጠው ይህ ክትባት የኮሺድ ፕሮቶኮል በጠበቀ መንገድ እንደሆነ በመረዳት ህብረተሰቡ የልጆችን ጤና ለመጠነቅ ሁሉም ቤተሰብ ህፃናትን እንዲያስከትብ ጥሪ አቅርበዋል።
በአስተዳደሩ በቅርቡ የፖሊዮ በሽታ መታየቱን ገልፀው በሽታውን ለመከላክል ወሳኝ የሆነውን ፖሊዮ ከመደበኛው ክትባት በተጨማሪ በዘመቻ መልክ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው ዛሬ የተጀመረው የክትባት ዘመቻ የ2014 የመጀመሪያ ዙር መሆኑን አስረድተዋል።በሽታውን ለመከላከልም ህፃናትን ማስከተብ ይገባል ብለዋል።


