ከድሬዳዋ ወደ ወሎ የተለያዩ ድጋፎችን ጭኖ የተነሳው መኪና በዛሬው እለት ኮምቦልቻ ደርሷል ።

    ከድሬዳዋ ወደ ወሎ የተለያዩ ድጋፎችን ጭኖ የተነሳው መኪና በዛሬው እለት ኮምቦልቻ ደርሷል ።
    በድሬዳዋ አስተዳደር የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲሁም ነዋሪነታቸውን በአሜሪካን ሀገር ያደረጉ በጎ-አድራጊ አካላትን በማስተባበር በሰሜን ወሎና አካባቢው በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን እርዳታ የሚውሉ የተለያዩ አልባሳት ፣ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች ፣ የምግብ ዱቄት የመሳሰሉትን ቁሳቁሶችን ትናንት በስፖርት ኮሚሽን በር ላይ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችና የድጋፍ አስተባባሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ግለሰቦች በተገኙበት ሽኝት መደረጉ ይታወሳል ።
    ይኸውም ድጋፍ ትናንት ከድሬደዋ ተነስቶ አዲስ አበባ በማደር ዛሬ ማምሻውን ኮምቦልቻ ደርሷል ። በሁለት ኤፍ-ኤሳር መኪና የተጫነው ይኸው ድጋፍም በነገው እለት ለተፈናቃሉ ወገኖቻችን የሚያደርስ ይሆናል !