በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኙ አጠቃላይ አመራሮች በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት በማካሄድ ይገኛሉ ።

    አሸባሪው የህወሀት ቡድን በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ ግልፅ ጦርነት በማወጅ ሀገር የማተራመስና የማፍረስ ሴራውን በማካሄድ ላይ ይገኛል ። አሸባሪ ቡድኑ በተለይም በአፋርና በአማራ ክልሎች ላይ ንፁሀን ዜጎቻችንን የመጨፍጨፍና ሀገር የማፍረስ ብሎም ዜጎችን የማፈናቀል ስራ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ይህንንም ታሳቢ በማድረግ እያንዳንዱ ክልል አካባቢውን መጠበቅና ሀገርን ከዚህ የጠላት ሴራ ለማምከን በዘመቻው ላይ መሳተፍ እንዲሁም የአሸባሪውን ሴራ ነዋሪው ህብረተሰብ አውቆትና ተረድቶት ይህንን የመታገል ስራ ህዝባዊ ማድረግ በሚቻልባቸው ዙሪያዎች አጠቃላይ አመራሩ ውይይት እያደረገ ይገኛል ።
    ከዚህ ባለፈም ሰራዊቱን በማንኛውም መንገድ ከመደገፍ አንስቶ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ዜጎቻችን የተለያዩ ድጋፍ በማድረግ ረገድ የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆን እንዳለበት በመድረኩ ላይ ተነስተዋል ።