በወቅቱ ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የተገኙት፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለተደረገው ድጋፍ በአስተዳደሩ ነዋሪዎች ስም ምስጋና አቅርበው፤ “በሁሉም ዘርፍ ለሰራዊቱ ደጀንነታችንን በማጠናከር፤ አሸባሪውን የህወኀት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድና፤ ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ማሻገር ከእያንዳንዳችን የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው” ብለዋል።
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ እና ድሬዳዋ የሚገኘው የምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል አዛዥ ኮሎኔል ብርሃኑ ዘውዴ ድጋፉን በጋራ የተረከቡ ሲሆን፤ የኒቆዲሞስ መታሰቢያ የወንድማማቾች እቁብ አባላት በቀጣይ ለሰራዊቱ ደጀንነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።


