በአሰተዳደራችን የተጀመረዉ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ላልተወሰነ ጊዜ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ እስከ ቀበሌ መዋቅር ባለው የአመራር አካላትን ያሳተፈ ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻው በዛሬው ዕለትም በተመረጡ የገበያ መዕከላትና ጎዳናዎች ተከናውኗል ።
    ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጅምሮ የአስተዳደራችን ትልቁ የገበያ መዕከል የሆነው ቀፊራን ጨምሮ በመልካ ጀብዱና በተለያዩ ጎዳናዎች ላይ የጽዳት ዘመቻ የተካሄደ ሲሆን የጽዳት ዘመቻውን በበላይነት የሚመሩት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከዲር ጁሃር ዛሬ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ ላይ እንደገለጹት በአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እስከ ቀበሌ ድረስ ባለው የአመራር ሙዋቅር የሚሳተፉበት ይህ የጽዳት ዘመቻ ዓላማ አድርጎ የተነሳው አመራሩ የሚያስተዳድራት ከተማ ጽዱ፣ ውብ እና ምቹ እንድትሆን የበኩሉን ሚና ለመወጣት ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ በአከባቢ ጽዳት ስራ ላይ አርዓያ በመሆን በህብረተሰቡ ዘንድ የተነሳሽነት ስሜት በመፍጠር ቁሻሻን የሚጸየፍ መህበረሰብ በማፍራት ጽዱ፣ውብ እና ለኑሮ ምቹ የሆነች ድሬዳዋን እውን ማድረግ ነው ።
    ክቡር ከንቲባው ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በተለይም በቀበሌ መዋቅር ውስጥ በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት ለአከባቢው ጽዳት ትኩረት በመስጠት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አከባቢን የማቆሽሽ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ከዚህ ጓንለጓን ግን የህብረተሰቡን አመለካከት በመቀየር በየጊዜው በሚከናወኑ የጽዳት ዘመቻዎች ላይ ተሳትፎውን በማሳደግ ለድሬያችን ሁለንተናዊ ዕድገት የበኩሉን ሃላፊነት መወጣት እንዲችል ከ አመራሩ የሚጠበቅ ትሊቁ ስራቸው ነው ብለዋል ክቡር ከንቲባው። የተጀመረው ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል።