የድሬዳዋ የብልጽግና ፓርቲ ወጣትና ሴት አደረጃጀቶች ኢትዮጵያን ከጁንታውና ከተላላኪው ሸኔ ለመጠበቅ ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ለመቆምና በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖቹን ለመደገፍ ቆርጠው መነሳታቸውን አስታወቁ
ዛሬ በኢትዮጠሊያን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አዳራሽ በተከናወነ የድሬዳዋ አስተዳደር የብልጽግና የወጣትና የሴቶች አደረጃጀት መድረክ ላይ ስለ ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ ገለጻ ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ኢትዮጵያ ለውጪ ጠላትም ሆነ ለውስጥ ተላላኪና ባንዳ የማትንበረከክ ሀገር መሆኗን ዳግም በአጭር ጊዜ አረጋግጠን ወደ ልማታችን መመለስ ይኖርብናል ብለዋል ፡፡
በከተማችን ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ሴራዎች በጁንታው ሲሰሩ ቆይተዋል ያሉት ኃላፊው እንደ ሀገርም የተጀመረውን ለውጥ ለመቀልበስና የሁላችንም የሆነውን የህዳሴ ግድብ ለማደናቀፍ ያልቆፈሩት ጉድጓድ ያልቧጠጡት ተራራ የለም ግን አልተሳካላቸውም ብለዋል ፡፡
አቶ ኢብራሂም በመልዕክታቸው መጨረሻ በአማራና በአፋር ክልል እየተፈጸሙ ያሉ ታሪክ ይቅር የማይላቸው ግፎች እንዲቆሙ ሁላችንም ከመከላከያ ጎን ልንሰለፍ ፣ የተፈናቀሉትን ልንደግፍ ፣ አካባቢያችንን ልንጠብቅ ፣በውስጣችን ያሉትን ጁንታዎችና ተላላኪዎች ልናጋልጥና ለጸጥታ አካላት አሳልፈን ልንሰጥ ይገባል ብለዋል ፡፡
ተሳታፊዎችም ለሀገር የሚሰሰት ነገር እንደሌለና በሞራል ፣ በገንዘብ ፣ አካባቢን በመጠበቅና እስከ ጦር ሜዳ በመሄድ ህይወታቸውን ለመሰዋት መዘጋጀታቸውን በመድረኩ አረጋግጠዋል ፡፡


