የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በሽብር ተግባር የተጠረጠሩ ከ208 በላይ ሰዎችን መያዙን አስታወቀ ፡፡

    ለሽብር ሊውሉ የተዘጋጁ የጦር መሳርያዎች ፣ የተለያዩ ሀገራት ብሮችና ሰነዶች ከተጠርጣሪዎቹ መኖርያ ቤት ከማህበረሰቡ እና ከጸጥታ አካላት በደረሱ ጥቆማዎች መያዙን ጨምሮ ገልፀዋል ፡፡
    የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከማህበረሰቡ እና ከጸጥታ አካላት የደረሱ ጥቆማዎችን መሰረት አድርጎ ባከናወነው የሁለት ቀናት ኦፕሬሽን 5 ሽጉጥ ፣ በርካታ ተቀጣጣዮች ፣ ላፕቶፖች ፣ የተለያዩ ሞባይል ቀፎዎች ፣ የጦር ሜዳ አቅጣጫ ጠቋሚዎች ፣ 151,000 ( አንድ መቶ አምሳ ሺህ) የሀገር ውስጥ የብር ኖቶች ፣ የውጪ ሀገር ገንዘቦች ፣ የቀድሞ የሀገር መከላከያ የደምብ ልብሶች ፣ ወታደራዊ የማዕረግ ምልክቶች ፣ ለስልጠና የሚያገለግሉ ቱታና ጫማዎች ፣ የትግራይ ክልልን ጨምሮ የተለያዩ አዳዲስ መታወቅያዎችና ሰነዶች በሽብር ተግባር ተጠርጥረው ከተያዙ ከ208 በላይ ግለሰቦች ቤት ውስጥ መገኘቱን ኮማንደር ገመቹ ካቻ የድሬዳዋ አስተዳር ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ለውጥ ስራ አመራር ዳይርክቶሬት ዳይርክተር አስታውቀዋል ፡፡
    ጁንታው ድሬዳዋን ባለፉት 27 ዓመታት ፋብሪካዎቿን ከጥቅ ውጪ በማድረግ ህዝቧን በድህነት አረንቋ ውስጥ የዘፈቀ ስርዓት ለመመለስ ከጀሌው ኦነግ ሸኔ ጋር በመሆን አባላትን በመመልመል ፣ በማስታጥቅና ለጥፋት በማሰማራት ሽብር ለመፈጸም ዝግጅት እንደ ነበር በምርመራ ማረጋገጡን ኮማንደሩ አስታቀው የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የድሬዳዋን አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ከህበረተሰቡ ና ከጸጥታ ኃይሉ ጋር የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ::