ኤልአውቶ ኢንጂነሪንግ የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብን ለሁለት አመት ስፖንሰር አደረገ ።

    ኤልአውቶ ኢንጂነሪንግ በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ የተለያዩ መኪናዎችን በመገጣጠም ከማቅረቡም በዘለለ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን በመስራት በሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት ላይ የራሱን አስተዋፆ በመወጣት ላይ ይገኛል ። ይኸው ድርጅት የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብን ለሁለት አመት ስፖንሰር ማድረግ ችሏል ። የድርጅቱ አመራሮችም ወደ ድሬዳዋ በመጡበት ጊዜም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
    የምስራቁ የሀገራችንን ክፍል በብቸኝነት የሚወክለው የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ በተለይም ስፖርት ክለቡ የድሬዳዋ ከተማን ብቻ ሳይሆን የምስራቁ የሀገራችን ክፍልን እንደሚወክልና ኤላውቶ ኢንጂነሪንግ አሁን ላይ ለክለቡ ስፖንሰር ከመሆኑም ባሻገር በቀጣይም በከተማው ላይ ለውጥን ሊያመጡ የሚችሉ የተለያዩ ስራዎችን ሊሰራ እንደሚችል ያላቸውን እምነት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር ተናግረዋል ።
    ኤልአውቶ ኢንጂነሪንግ ለድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ የ 10 ሚሊዮን ብርና 54 ሰው የመጫን አቅም ያለው ዘመናዊ ባስ ለዋናው ቡድን ለመግዛት የ2 አመት ስፖንሰር-ሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል በዚሁም በፕሮግራም ላይም ንግግር ያደረጉት የኤልአውቶ ኢንጂነሪንግ ድርጅት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ በቀለ አቤቤ ትክክለኛውን ክለብ ስፖንሰር ለማድረግና በተለይም ደግሞ የሀገራችን የስፖርት እድገት ለማገዝ የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብን ስፖንሰር በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ዋና ስራ-አስኪያጁ ተናግረው ክለቡና የከተማ አስተዳደሩ ለሰጣቸው እድልም አቶ በቀለ አቤቤ አመስግነው አሁን ላይ የተፈራረሙት ስምምነት የመጀመሪያ ሲሆን በቀጣይም ከክለቡና ከከተማው ጋረ ያላቸውን አጋርነት ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ እንሚቀጥልም በእለቱ ተናግረዋል፡፡
    የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ የቀድሞ ስምና ዝናውን ለመመለስ ሁሉም የስፖርት ቤተሰብኖች እንደ ኤሌውቶ ሁሉ በመደገፍ በማበረታታት በአይነትም ሆነ በገንዘብም ከስፖርት ክለቡ ጎኑ በመቆም ሁላችንም የድሬዳዋ ስፖርት ክለብን በመደገፍ የአሸናፊነት ተምሳሌት እንዲሆን መንቀሳቀስ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊና የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሱልጣን አሊዪ ተናግረዋል ።
    ኤልአውቶ ለድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ካደረገው ስፖንሰር በተጨማሪም ለድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ሁለት የሞተር ተሸከርከሪዎችንና ሌሎች ድጋፎችን ማድረግ ችሏል ።