የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ 13ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል ።

    የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ 2013 ዓ.ም ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎችና ፕሮግራሞች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 3559 ተማሪዎችን አስመርቋል ። በዩኒቨርሲቲው የመማክርት ጉባኤ ፀድቆላቸው ለምርቃት የበቁት ተማሪዎች በመደበኛ በተከታታይና በክረምት በሰባት የትምህርት መርሀ-ግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩና በመጀመሪያ ዲግሪም 3431 ፣ በሁለተኛ ዲግሪ 128 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 1016 የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ የተገለፀ ሲሆን ከተመራቂ ተማሪዎች መካከልም ከተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ጎረቤት ሀገራት የተውጣጡ 22 ተማሪዎችም ይገኙበታል ።
    በዚሁ የምረቃት ስነ-ስርአት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የዲሞክራሲ ማእከል ሚኒስቴር እንዲሁም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሀ በሀገራችን ላይ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ባለፍት ሶስት አመታት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ያሉትን ችግሮች በመለየትና ለችግሮቹም መፍትሄ በማበጀት ተማሪዎች በመቻቻል ፣ በመተሳሰብ ፣ በአንድነት እንዲሁም በመደጋገፍ መንፈስ ለሀገራቸው እድገት በጋራ እንዲሰሩ ለማስቻል እንደ ተቋም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
    ተመራቂ ተማሪዎች በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ መልካም ጊዜ እንዲሆንላቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተመኝተው በተለይም ግን በሚሄዱበት ብሎም የሚኖሩበትን አካባቢ ሰላም ለመጠበቅና አካባቢውን ለማገዝ ከተለያዩ የፀጥታ ሀላፊዎችና ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ሰርጎ ገቦች እንዳይኖሩ በማድረግ ሀገራችንና አካባቢያቸውን መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረው ኢትዮጲያዊ ባህላችን የሆነውን የመተጋገዝና የመረዳዳት ባህላችንን የተፈናቀሉ ወገኖቻችንንም በመርዳትና በማገዝ ማስቀጠል እንደሚገባም አቶ ከድር ጁሀር በእለቱ ተናግረዋል ።
    የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋት አንፃር አሁን ላይ 12.560 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ 1.463 ተማሪዎችን በሁለተኛ ዲግሪ በአጠቃላይ ደግሞ ከ 14 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝና በበጀት አመቱም 6 ስርአተ ትምህርቶችን በቅድመ ምረቃ 22 ስርአተ ትምህርቶችን ደግሞ በድህረ ምረቃ ባለድርሻ አካላትና ሀገር አቀፍ ባለሞያዎችን ባሳተፈ መልኩ መቅረፅ መቻሉን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ተናግረው የትምህርት ፍትሀዊነትን ትኩረት በማድረግ ከ 100 በላይ ተመራቂ ተማሪዎች ሙሉ ልብስ ወጪ በማድረግ ብሎም ለሴት ተማሪዎችም የተለያዩ ስልጠናዎች መሰጠት እንደተቻለና ለአካባቢው ማህበረሰብም የነፃ የትምህርት እድል መሰጠት መቻሉንም ዶክተር ኡባህ አድም በምረቃት ስነ-ስርወቱ ላይ ተናግረዋል ።
    በእለቱ ተመራቂ የሆኑ ተማሪዎች በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው የነበራቸው የትምህርት ቆይታ ጥሩ እንደነበር ተናግረው በቀጣይም በሚሰማሩበት የስራ መስክ ነዋሪውን ህብሩተሰብ በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ተመራቂ ተማሪዎቹ ተናግረዋል ።