በድሬዳዋ አስተዳደር የ2013 የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ማዕከላትን ከድሬዳዋ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍና ከአስተዳደሩ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቂያስ ታፈሰ ጋር ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ በሰጡት መግለጫ ምንም እነኳ በጦርነት ውስጥ ብንገኝም ባለፈው ዓመት በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክኒያት ማድረግ ያልቻልነውን የ12ኘ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ያለምንም የጸጥታ ችግር በሁሉም መዕከላት እየተከናወነ እንዳለ መመልከታቸውን ተናግረዋል ፡፡
ከንቲባ ከዲር ጁሐር ከትምህርት ሚኒሰቴር ሚኒስትር ፐሮፌሰር ብርሀኑ ጋር ባደረግነው የዙም ስብሰባ ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለፈተናው ትኩረት በመስጠት ድጋፍ እንዲደረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው ብለዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ክፍል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ነጋሽ በድሬዳዋ አስተዳደር የ2013 ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ለመፈተን ከተመዘገቡሁለት ሺህ አራት መቶ ሀያ አራት (2424 )መካከል ሁሉም ለመፈተን በአራቱም የፈተና ማዕከላት መገኘታቸውን አረጋግጠዋል ፡፡
አቶ ሳሙኤል አክለው እነደ ገለጹጽ ፈተናዋውን ለማስፈጸም አራት የፈተና መዕከላት ኃላፊዎች ፣ ሀያ ሱፐር ቫይዘሮችና ስድሳ ፈታኝ መምህራን ተሳፊዎች መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡


