አላግባብ የዋጋ ንረት ለመጨመር የሚጥሩ አካላት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ
በአስተዳደሩ የሸቀጦችና የአገልግሎት የዋጋ ንረትን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሀይል ውይይት አካሂዷል ፡፡ በውይይቱም የሚታዩ የዋጋ ንረቶችን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በተለይም ከመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ጋር በተያያዘ እጅግ የገነነ ችግር መኖሩ ተመላክቷል፡፡ በነዳጅ አቅርቦት ረገድም እንደዚሁ ከፍተኛ ችግር መኖሩ የተገለጸ ሲሆን የሚመለከተው አካል ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት ከባለድረሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት መስራት…


