በድሬዳዋ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከአስተዳደሩ ሴክተሮች እና የከተማ ቀበሌዎች ጋር ለውጥ ስራ አመራሮች ባካሄደዉ ውይይት ላይ የድሬ ደዋ አስተዳዳር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አቡበከር አብዶሽ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ፐብሊክ ሰርቫንቱ ህብረተሰቡ የሚፈልገዉን አገልግሎት በጥራትና በፍጥነት እንዲያቀርብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ አቡበከር አክለዉም በየተቋማቱ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ብሎም ህብረተሰቡ ከመንግስት የሚፈልገዉን አገልግሎት በጥራትና በፍጥነት ለማቅረብ እንዲቻል ሁሉም ተቋማት እንደየስራ ዘርፋቸዉ የአገልግሎት አሰጣጣቸዉን የሚያቀላጥፉ የለውጥ መሳሪያዎች በአግባቡ ተጠቅመዉ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለዉ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በሁሉም ተቋማት የሚገኙ ለውጥ ስራ አመራሮች በለውጥ መሳሪያዎቹ ላይ ተቀራራቢ ዕዉቀት ኖሮዋቸዉ እንዲሰሩ ለማድረግ ታስቦ ይህ የዉይይት ስልጠና መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡


