በአስተዳደሩ የሸቀጦችና የአገልግሎት የዋጋ ንረትን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሀይል ውይይት አካሂዷል ፡፡
በውይይቱም የሚታዩ የዋጋ ንረቶችን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት የተገመገሙ ሲሆን በተለይም ከመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ጋር በተያያዘ እጅግ የገነነ ችግር መኖሩ ተመላክቷል፡፡
በነዳጅ አቅርቦት ረገድም እንደዚሁ ከፍተኛ ችግር መኖሩ የተገለጸ ሲሆን የሚመለከተው አካል ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት ከባለድረሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት መስራት እንደሚገባው ተገልጸል፡፡
የቅዳሜና እሁድ ገበያ መጀመሩ በዘርፉ በመልካም አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በቀጣይ በቀበሌዎችና በዋና ዋና አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ በአስተዳደሩ የሚስተዋሉ የሸቀጦችና የአገልግሎት የዋጋ ንረትን ለመከላከል ቢሮው ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደሚሰራ ተናግረው ህብረተሰቡን ጨምሮ የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


