የአሸባሪውን የህወሀት ቡድን ሴራ ለማጋለጥና ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ለመግለፅ የተዘጋጀ ውይይት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በዛሬው እለት ተካሂዷል ። በዚሁም የውይይት መድረክ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በተለይም አሸባሪው ቡድን ባለፍት ሶስት አመታት ሀገራችን ኢትዮጲያን ለማፍረስ ብሎም ለውጡን ለማደናቀፍ በርካታ ስራዎችን መሰራቱን እንዲሁም አሸባሪው የህወሀት ቡድን በሀገራችን ላይ እያካሄደ ያለውን ሴራ ለንግዱ ማህበረሰብ ገለፃ አድርገዋል።
በድሬደዋ አስተዳደር አሸባሪውን የህውሃት ቡድንን ለመደገፍ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ 250 በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተናግረው ከተማዋ ካላት የመልካ ምድር አቀማመጥ አንፃር እነዚሁ አካላት እኩይ ሴራቸውን ለማስፈፀም አቅደው እንደተንቀሳቀሱም አቶ ከድር ተናግረዋል።
የከተማዋን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚያደንቁ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ ተናግረው ይህንኑ ስራም አጠናክሮ ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ በገንዘብ ከሚያደርጉት ድጋፍ በዘለለ በአይነትም ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን ከሁሉም በላይ ግን ሀብትና ንብረት ሊኖር የሚችለው ሀገር ስትኖር እንደሆነና ባለሀብቶቹም ኢትዮጲያን ለማዳን በሚደረገው ጥረት ሁሉ በገንዘብና በአይነት ከሚያደረጉት አስተዋፅዖ በተጨማሪ ግንባር በመገኘትም ለመዋጋት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ፣ ነዋሪዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ባለሀብቶች ለምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል በርካታ ድጋፎች በማድረጋቸው የሆስፒታል አዛዥ ኮረኔል ብርሀኑ ዘውዴ ምስጋናቸውን አቅርበው ሀገርን ከጠላት ሀይል በጋራ በመሆን መከላከል እንደሚገባም ኮረኔል ብርሀኑ በውይይት መድረኩ ላይ ተናግረዋል ።


