ኢትዮጲያን ለማዳን በሚደረገው ጥረት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብ ተናገሩ ።
የአሸባሪውን የህወሀት ቡድን ሴራ ለማጋለጥና ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናቸውን ለመግለፅ የተዘጋጀ ውይይት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በዛሬው እለት ተካሂዷል ። በዚሁም የውይይት መድረክ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በተለይም አሸባሪው ቡድን ባለፍት ሶስት አመታት ሀገራችን ኢትዮጲያን ለማፍረስ ብሎም ለውጡን ለማደናቀፍ በርካታ ስራዎችን መሰራቱን እንዲሁም አሸባሪው የህወሀት ቡድን በሀገራችን ላይ እያካሄደ ያለውን…


