በኢትዮጵያ የአርመን አምባሳደር አርቲም አዝናሪዮን
አምባሳደሩ በድሬደዋ አስተዳደር በመገኘት የአርመን ማህበረሰብ የተለያዩ ቅርሶችን እና በአስተዳደሩ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸው የተመለከቱትን ጉዳይ ሲያስረዱ በድሬደዋ በርካታ የውጭ ሀገራት ዜጎች አሻራቸው ያረፈባት ከተማ መሆኗን መገንዘብ መቻላቻን ተናግረዋል፡፡
ይህ ለከተማዋ ልዩ መገለጫ መሆኑን ገልጸው እንዲህ አይነት ለቱሪስት መስህብ የሚሆኑ ቅርሶችና ስፍራዎች በሚገባ ተጠብቀው ከመልማት ባለፈ ተገቢው የማስተዋወቅ በስፋት መሰራት እንደሚገባው ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
አክለውም የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሮቿን በራሷ አቅም መፍታት እንዳላት ገልጸው በድሬደዋ የተመለከቱት ሁኔታ ሰላማዊ ሆኖ ማግኘታቸውን አስረድተዋል፡፡
በሌላ በኩል የድሬደዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ የአምባሳደሩ ጉብኝት አንዳንድ የውጭ ሀገራት በተሳሳተ መልኩ ዜጎቻቸውን ከአገራችን እንዲወጡ እያደረጉ ባሉበት ሰአት መካሄዱ ሁኔታውን በተለየ መንገድ ለማመላከት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ሁላችንም የሀገራችንን ገጽታ ከመገንባት ረገድ ባለን ሞያና ባለን አቅም የበኩላችንን ማበርከት ይገባናል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በአስተዳደራችን ለውጭ ሀገር ዜጎች እና ለሀገር ውስጥ ጎብኚዎች የቱሪዝም መስህብ የሆኑ ስራዎችን ለማስተዋወቅ በስፋት እንደሚሰራ ገልጸዋል


