ከድሬዳዋ ፖሊስ የተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ

    የድሬዳዋ ፖሊስ እንዳስታወቀው ማንኛውም በድሬዳዋ ከተማ እና ገጠር ውስጥ የሚገኝ ግለሰብ ፣መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትና መ/ቤት በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ፍቃድ ቢኖረውም ባይኖረውም በአቅራቢያው በሚገኝ የቀጠናው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በግንባር በመሄድ ማስመዝገብ እንዳለበት አሳስቧል፡፡
    ፖሊስ እንዳስታወቀው ከህዳር 2 ቀንእስከ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ፣ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትና መ/ቤት በእጁ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ሳያስመዘግብ የቀረ ከሆነ በህግ አግባብ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወሰድ የድሬዳዋ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡