“በብሔር ላይ እየተሠራ ያለውን የተዛባ ትርክት ለመቀልበስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን ሚና መጫወት አለበት”፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
*********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በብሔር ላይ እየተሠራ ያለውን የተዛባ ትርክት ለመቀልበስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን ሚና መጫወት እንዳለበት አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ተከታዩን መልእክት አስተላልፈዋል።
“ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፣ በሩቅ እና ቅርብ ያሉ፣ የሀገራችንን በጎ የማይፈልጉ አካላት ያለ የሌለ ሀብትና ጉልበታቸውን ተጠቅመው፣ በሀገራችን ላይ የተበላሸ ትርክትን የመጫን ጦርነት መክፈታቸውን አንዘንጋ።
በብሔር ላይ እየተሠራ ያለውን የተዛባ ትርክት ለመቀልበስ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን ሚና መጫወት አለበት።
በኅብረ ብሔራዊ አንድነት የራሳችንን ታሪክ እኛው እንሠራለን፤ እኛው እንጽፋለን!”


