በመንግስት ኮሙዩኒኬሽን የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ሲሳይ የ2014 ዓ.ም እና የ60 ቀን እቅድ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን እቅዱ የBSCን ፎርማት በተከተለ መልኩ መዘጋጀቱ ጥሩ መሆኑ በግምገማው ታይቷል።
ተቋሙ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ከአማረኛ ቋንቋ በተጨማሪ በኦሮምኛና በሱማሌኛ ቋንቋ የሚታተሙ የድሬ ጋዜጣ መጀመሩ ጥሩ ሆኖ ሳለ በከተማ የሚከናወኑ ተግባራት ብቻ ማተቱ እንደ ክፍተት የታየ ሲሆን የገጠሩ የልማት ስራዎችን በስፋት የሚያሳይ መሆን እንደሚገባው በግምገማው ተጠቁማል።
ቢሮው ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ግንኙነት ላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባው በመጥቀስ በተለይም ከብዙሀን መገናኛ ድርጅት ጋር በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባው እንዲሁም በየቀበሌው ከሚገኙ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎችን ብቃት ለማሻሻል ስልጠናዎችን መበስጠት በጋራ ተደጋግፎ መስራት እንደሚገባ ተጠቁማል።
በመጨረሻም በአስተዳደሩ አስተናጋጅነት የሚካሄደውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አከባበር ከከተማ ስራ አስኪያጅና ከሌሎች ተቋማት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ በግምገማው በተቋሙ ላይ በተነሱ ሀሳቦች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በጋዜጣ ዝግጅቱ የተነሳ ሀሳብ እንደ ተቋም በመውሰድ በቀጣይ እንደሚስተካከል ምላሽ በመስጠት መሰል ተቋማት ጋር በቅንጅት ከመስራት አንፃር ቢሮው ከተቋቋመበት ተግባርና ኅላፊነት በተጨማሪ የሚዲያ ስራ በመስራት ይገኛል በማለት በቅንጅት መስራትን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም የቀበሌ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎ አደረጃጀቱ በራሱ ያመጣው ችግር ወደፊት የሚፈታ ሲሆን ተቋሙ ብቃት ለማሻሻልና አቅማቸውን በስልጠናዎች የመገንባትና በማቴሪያል ድጋፍ የማድረግ ተግባራትን ከዚህ ቀደሙ በተሻለ እንሰራለን ብለዋል።


