የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በጥቅምት ወር ከ240 ሚሊዬን
ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ታወቀ፡፡
****************************************************
የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ገቢ በመሰብሰብ ለልማት እንዲውል የሚያደርግ ተቋም ነው፡፡ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ባስቀመጠው የአስር ዓመት የገቢ የልማት ዕቅድ መሰረት የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየሰራ እንደሚገኝ የባለስልጣን መ/ቤቱ ማኔጅመንት ባደረገው ግምገማ ታውቋል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ በ2014 በጀት ዓመት ከመንግስት ታክስና ከማዘጋጃቤት ገቢ 2.3ቢሊዬን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ባለስልጣን መ/ቤቱ የበጀት ዓመቱ የጥቅምት ወር ዕቅድ አፈፃፀም በገመገመበት ወቅት ታውቋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጥቅምት ወር ብር 239,032,243.52 ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 240,372,231.00 በመሰብሰብ የእቅዱን 100.56በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡
ይህ አፈፃፀም ከዕቅዱ አንፃር 0.56በመቶ ወይም በብር 1,339,987.48 ብልጫ እንዳለው ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል ይህ አፈፃፀም ከባለፈውበጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 50.56በመቶ ወይም በብር 80,721,982.99 ብልጫ እንዳለው ታውቋል፡፡
ለዚህ ዕቅድ ስኬት በዋናነት የደረሰኝ ቁጥጥር ፣ የእዳ ክትትል እና የኦዲት ሽፋንን በማሳደግ የመጣ ሲሆን በቀጣይም ይህንን በተሻለ አፈፃፀም አጠናክሮ ለማስቀጠል የአመራሩ ፣ የፈፃሚውና የታማኝ ግብር ከፋዬች ጥምረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳበት ተመላክቷል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ገቢውን በተሻለ መንገድ ለማስቀጠል በዘንድሮ በጀት ዓመት በመደበኛና በካፒታል ፕሮጀክት ተይዘው ወደ ስራ የተገባባቸው የሲስተም ግንባታና የደረጃ ‘‘ሐ’’ የቀን ገቢ ግምትና የደረጃ ክለሳ ስራዎች በሙሉ አቅም ወደ ስራ መገባት እንዳለበት በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር የህግ ተገዢነትን በመጠበቅ መሰራት እንዳለበት ታውቋል፡፡
ምንጭ፡-ከአስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን


