የድሬዳዋ ህዝብ ጥያቄ የነበረው የለገሀር አደባባይ ባቡር በቦታው በዛሬው እለት ተመልሶል።
እ.ኤ.አ አቆጣጠር ታህሳስ 22 ቀን 1902 ከጅቡቲ የተነሳው ባቡር በርካታ የምድር ባቡር ኩባንያና የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸውን ሰራተኞችን አሳፍሮ አመሻሽ ላይ ድሬደዋ የምድር ባቡር ኩባንያ ዋና ጽ/ቤት ያለበት ቦታ ደረሰ ለከተማዋም መመስረት ዋንኛ ምክንያት ሆነ።
በተለያዩ ምክንያቶች ከአደባባዩ ላይ የተነሳው ባቡር ወደ ቀድሞው ቦታው በዛሬው እለት በአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር አማካኝነት ወደ ቀድሞ ቦታው ተመልሷል።
በመልሶ ተከላ ስነ-ስርዓቱ ላይ ከንቲባ ከድር እንደተናገሩት የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ የድሬዳዋ ማህበረሰብ መገለጫ የሆነው ምድር ባቡር አደባባይ በቦታው ከመመለስ ባለፈ በቀጣይ ህዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዋች በተዋረድ ምላሽ እንሰጣለን ብለዋል።


