የ06 ቀበሌ ሰራተኞች የደሞዛቸውን 15% ለጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ፡

    የ06 ቀበሌ ሰራተኞች የደሞዛቸውን 15% ለጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ፡
    የድሬዳዋ አስተዳደር ቀበሌ 06 ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ዉይይት ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የደሞዛቸው 15% ድጋፍ አደረጉ፡፡
    በሀገራችን አትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሰሜን እዝ ላይ አሸባሪዉ የህዉዋት አጥፊ ቡድን ጥቅምት24/2013ዓ.ም ጥቃት ማድረሱ ይታወሳል እንዲሁም በንጹሃን ዜጎች ላይ ንብረት የማዉደም ህይወት የማጥፋት እና የዜጎችን የስነ ልቦና ቀዉስ ዉስጥ በማስገባት እኩይ ድርጊት በመፈጸም ላይ ይገኛል ይህን አጥፊ ቡድን ከሀገራችን መጥፋት አለበት በማለት የ06 ቀበሌ ሰራተኞች ዉይይት አደረጉ፡፡
    በዉይይቱም ላይ የሀገርን ህልዉና ለማስጠበቅ ቀን ከሌት ከሚለፋዉ የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት ጎን ለመቆም የ06 ቀበሌ ሰራተኞች ከደሞዛቸው 15% ድጋፍ አድርገዋል፡፡
    በቀጣይ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርጉና አካባቢያቸዉን በንቃት ለመጠበቅ ዝግጁ መሆናቸዉን በመግለጽ መንግስት አሸባሪዉን የህዉዋት ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ በመገኘቱ እኛም ከጉኑ ነን ብለዋል ፡፡
    ምንጭ፡- 06 ቀበሌ ኮሚኒኬሽንና ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ