<<ኪነ-ጥበብ ለአገር ፍቅርና ህዝባዊ አንድነት>> በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ምድር ባቡር አደባባይ የኪነ ጥበብ ኮንሰርት በድምቀት ተካሄደ።

    <<ኪነ-ጥበብ ለአገር ፍቅርና ህዝባዊ አንድነት>> በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ምድር ባቡር አደባባይ የኪነ ጥበብ ኮንሰርት በድምቀት ተካሄደ።
    የአገር ፍቅር እና ህዝባዊ አንድነት የሚያቀነቅኑ ለአገር ጥሪ አንድ አካል የሆነው የኪነ -ጥበብ ኮንሰርት በድሬዳዋ መገለጫ በሆነው ጣፋጭ ምግቦችና ፈጣን የዛፍ ስር ምግቦች በልዩ ሁኔታ የቀረቡ ሲሆን በኮንሰርቱ የአስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጆሀርና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዋች ታድመዋል።
    በኪነ -ጥበብ ኮንሰርቱ የድሬደዋ ከንቲባ ከድር ጆሀር ለታዳሚዋች ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት ጥበብና ፀሐይ ከወደ ምሥራቅ ይፈልቃሉ የሚለው አባባል እውነት ነው እኛም ጥበብን ተጠቅመን ከተማዋን ከርዥራዥ ጁንታና ከቆሻሻ ማፅዳት ይጠበቅብናል ብለዋል።
    ከንቲባ ከድር አክለውም እንደተናገሩት ህዝብ አምኖ እስከመረጠን ድረስ በስልጣን ቆይታችን ማህበረሰቡን ለማገልገል በዋናነት ከያዝናቸው ስራዋች አንዱና ዋንኛው ተግባር የፅዳት ዘመቻ በመሆኑ ዛሬ ለ9ኛ ጊዜ አካሄደናል። ማህበረሰቡ የሚያደርገው አስተዋፅኦ የጎላ በመሆኑ በቀጣይ በሚኖረው የፅዳት ዘመቻ በአካባቢያችን ሁሉ በጋራ እንሳተፍ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
    ከንቲባ ከድር ከዚህም ጋር አያይዘው በሌላ ቦታ ሆነው በሶሻል ሚዲያ የከተማዋን እድገት የማይፈልጉና ወደኋላ እንድትሄድ የሚፈልጉ ስላሉ እነሱን ሳንሰማ ፍቅራችንና አንድነታችን እንዲሁም አብሮ የመብላት የመስራት ባህላችንና ልማዳችንን ይዘን ከናንተ ጋር ተደጋግፈን ከተማችንን ወደ ከፍታ ማማ እናደርሳታለን ብለዋል።
    በኮንስርቱ የታደሙ ነዋሪዋችም በሰጡት አስተያየት አስተዳደሩ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የድሮዎ ድሬዳዋ እንድናስታውስ ያደረገ ነው በማለትዋ በቀጣይ ከአስተዳደሩ የሚመቻቹ እንቅስቃሴዋች በመደገፍ ለድሬዳዋ እድገት የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል።
    በትዕግስት ቶሎሳ
    ፎቶ፦dira mayor office