ለ9 ዙር የፅዳት ዘመቻ በዛሬው እለት ተካሂዷል ።

    ለ9 ዙር የፅዳት ዘመቻ በዛሬው እለት ተካሂዷል ።
    በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአት ጀምሮ ከሰኢዶ እስከ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከድል-ጮራ እስከ ደቻቱ ድረስ ባሉት አካባቢዎች ላይ የፅዳት ዘመቻው የተካሄደ ሲሆን በዚሁም የፅዳት ዘመቻ ላይ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮችና ፣ የሴክተር ተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች ፣ የድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ፣ በበጎ-አድራጎት ስራዎች ላይ የተሰማሩ አካላት ብሎም የከተማዋ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።
    በዚሁ የፅዳት ዘመቻው ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በተለይም የፅዳት ዘመቻው በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በየሳምንቱ መካሄዳቸው ከተማዋ ፅዱና ውብ ትሆን ዘንድ አይነተኛ አስተዋፆ እንደሚኖረው ተናግረው አሁን ላይም በከተማዋ ላይ በየሳምንቱ እየተካሄደ ያለው የፅዳት ዘመቻ በቀጣይም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በነቂስ በመውጣትና አካባቢያቸውን በማፅዳት ሊሳተፍ እንደሚገባም ነው የተናገሩት ።
    የፅዳት ዘመቻው በቀጣይ ሳምንትም ቀጣይነት እንደሚኖረውም ታውቋል ።