ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን፤ አመሻሹን በ06 ቀበሌ ቀፊራ ገበያ ውስጥ የሚገኙ መንገዶችን ቅኝት አድርገዋል።
ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን፤ አመሻሹን በ06 ቀበሌ ቀፊራ ገበያ ውስጥ የሚገኙ መንገዶችን ቅኝት አድርገዋል። ከዚህ ቀደም በሳምንታዊ የፅዳት ዘመቻ ላይ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፤ የቀበሌው ፅ/ቤት ከደንብ አስከባሪና ከፀጥታ አካላት ጋር በሠራው የግንዛቤና ህግ የማስከበር ስራ፤ ከመኖሪያ ቤቶች በሚለቀቅ ፍሳሽ ቆሻሻ ምክንያት ይበከሉ የነበሩ የገበያው መንገዶች መሻሻል እንደታየባቸው ተመልክተዋል። ምንጭ፦ከንቲባ ጽ/ቤት


