የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ማኔጅመንትና ሰራተኛው ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የስንቅ በማዘጋጀት ኘሮግራም ድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ክድር ጁሀር እና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንዲሁም የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ አቶ ኑረዲን አብደላና ማኔጅመንት አባላት በኘሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የስንቅ ዝግጅት ስነ-ስርአቱ ላይ እንደተናገሩት ይህ በጎ ተግባር በማበረታታትና በመደገፋቸው እንዲሁም ሰራተኞቹ ይህንን በማድረጋቸው በአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል፡፡ እንዲሁም በርካታ ሴቶች እና ወንዶች ደጀንነታቸውን ባሳዩበት ዕለት ለጀግኖች የሚሆን ስንቅ ተዘጋጅቷል፡፡በፕሮግራሙ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ተገኝቷል፡፡ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በዕለቱ ንግግራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በግንባር በመገኘት ጦሩ ለመምራት ያሳለፉትን ውሳኔ ተከትሎ ከፍተኛ መነሳሳት መፈጠሩን አውስተው ወራሪውን አሸባሪ ድል ለማድረግ የምንችል ወደ ጦር ግንባር ስንሄድ የልማት ጉዳያችንም በተጓዳኝ ማስኬድ አለብን ብለዋል፡፡
ሁላችንም በተሰማራንበት መስክ ታሪካዊ ድርሻ መወጣት አለብን ሲሉም አክለዋል፡፡
ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ስንቅ ዝግጅት ኘሮግራም 10 ኩንታል የበሶ እህል 1600 ድርቆሽ እንጀራ፣ 20 ካርቶን ቴምር እንዲሁም አንድ የማኔጅመንቱ አባል በራስ ተነሳሽነት ባሰባሰበው 5ካርቶን እና 5 ጣሳ ቴምር በተቋሙ ስም የለገሱ ሲሆን የቢሮው ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኛች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ይህ ሲያንስበት ነው በሚል ከወት ደሞውዛቸው አመራሩ 20% እና ሰራተኛው 10% የደሞወዙን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል።
በተመሳሰይ የቢሮ ማኔጅመንትአባላትና ሰራተኛው ከአማራ እና አፋር ክልል ለተፈናቀሉ አካላት የልባሽ ጨርቆችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማሰባሰብ ጀምረዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንዲሁም የከተማችን ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር በግንባር ቀደምትነት ለሀገራቸው ክብር ለመዥመት በወሰኑበት ውቅት እዚህ ተቀምጬ ሀገሬ ስትወረር ማየት አልፈልግም ያሉ ሰራተኞች በክብር እንግዶች እና በትቋሙ ሰራተኞች ፊት ለመዝመት ቃል ገብተዋል
ምንጭ Dire Dawa Agriculture Bureau


