የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር የኤኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ጋር በመተባበር በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ክበባት አመራርና ሱፐርቫይዘሮች የፈጠራ ስራን ባህል ለማጎልበት ስራ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::
በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀዲ መሐመድ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለሁሉለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ እንደሆነ አውስተው ዘርፉ ለድሬዳዋ እድገት ሊያበረክት የሚችለውን አስተዋጽኦ በሚገባ ለመጠቀም የሚያችሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶችን ለማሳደግ የሚያግዙ እቅዶች ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡
የፈጠራ ስራዎችን በትምህርት ቤት ደረጃ በስፋት እንዲተገበሩ ለማስቻል ዳይሬክቶሬቱ ወደፊት ከተለያዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራ ኢንጂነር መሀዲ አስረድተዋል ፡፡


