የኢፌዴሪ ሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዳ/ር ኤርጎጌ ተሰፋዬ በድሬዳዋ የአካባቢ የማህበረሰብ ሮንድ ጥበቃ ለሌሎችም ምሳሌ መሆን የሚችል ነው አሉ::

    ክብርት ሚንስትሯ በድ/ዳ ወጣቶችና የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎች አከባቢን በመጠበቅ እረገድ እያከናወኗቸው ያሉ የሮንድ ጥበቃ ተግባራትን ተዟዙረው ጎብኝተዋል::
    የኢፌዴሪ ሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤረጎጌ ተሰፋዬ በድሬዳዋ ከተማ ትላንት ምሽት ላይ በተለያዩ መኖሪያ አካባቢዎች ተዟዙረው ወጣቶችና የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎች እያከናወኑት ያለውን የአካባቢ የሮንድ ጥበቅ ስራዎች ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
    ሚንስትሯ ከጉብኝታች መጠናቀቅ በሃላ በሰጡት አስተያየት የድ/ዳ ወጣቶችና ቀሪ የማህበረሰብ ክፍሎች አካባቢን ከሽብርተኞችና ወንጀል ፈፃሚዎች ለመጠበቅና ለመከላከል ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የምሽቱ ብርድ ሳይበግራቸው እየሰሩት ያለው ስራና ተግባር እጅግ የሚያስመሰግንና ለሌሎችም አርያነት ያለው ሆኖ እንዳገኙት ተናግረዋል::
    ሚንስትሯ አያይዘውም የፍቅር እና የመቻቻል ከተማ የሆነችው ድሬዳዋ ከተማ ሰለሟ ይበልጥ የተጠበቀና ፀጥታዋ የተረጋገጠ እንዲሆን መላው ህብረተሰብ የፖሊስ አጋርነቱን ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል::
    በድሬደዋ በሁሉም የከተማና ገጠር ቀበሌዎች በማ/ብ አቀፍ የፖሊስ አገሌግሎት አማካኝነት ወጣቶች ተደራጅተው አካባቢያቸውን የመጠበቅ ተግባር እያከናወኑ ያሉ ሲሆን ይሄውም በቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል ወጣቶች አካባቢውን ለመጠበቅ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ እንደ ሀገር በምሳሌነት ተወስዶ መጎብኘቱ የሚታወስ ነው ።
    ምንጭ ድሬ ፖሊስ