የ16ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ አገር አቀፍ የወጣቶች ሲምፖዚየም <<ወጣትነቴን ለሀገሬ >>በሚል መሪ ቃል በዓሉ በሚከበርባት ድሬደዋ ተካሄደ።

    የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር በሲምፖዚየም ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በሀገር ወዳድነት እና በባለቤትነት ስሜት በመነሳሳት በኢትዮጵያ ሰላም፣እድገትና ብልፅግና እንዲሁም አንድነት አብሮነት ላይ ከእስከዛሬው የተሻለ አስተዋጽኦ እንድታበረክቱና የዜግነት ግዴታችንን እንድትወጡ ሲሉ ለወጣቶች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
    በ16ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው አገር አቀፍ የወጣቶች ሲምፖዚየም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ዳ/ር ኤርጎጌ ተሰፋዬ እንደተናገሩት በዚህ አኩሪ ታሪካዊ ገድል ቀን የኢትዮጵያ ወጣቶች ሚና እጅግ የላቀና በታሪክ ተሰንዶ ለትውልድ የሚተላለፍበት ዳግመኛ አደዋ ባለቤት የሚያደርጋቸውና ወቅቱ የጣለባቸውን ታሪካዊ አደራ በሚገባ የተወጡበት ጊዜ ነው ብለዋል።
    ክብርት ሚንስተሯ ዳ/ር ኤርጎጌ ከዚህ ጋር አያይዘው ይህ የመጣብን ፈተና እና የተጋረጠብን ችግር የበለጠ አንድ እንድንሆንና እንድንበረታ አደረገን እንጂ ጠላቶቻችን እንደተመኙት አልተበታተንም፣ አልከፉፈሉንም ወደፌትም ለእኩይ አላማቸው የማንበረከክና እራሳችንን አሳልፈን የማንሰጥ መሆናችንንና በአለም አደባባይ ሀገራችንን ከፍ እንድትል አድርጎታል ብለዋል።
    የኢፌዴሪ ብልፅግና ፖርቲ የወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፈ በወጣት አክሊሉ ለገሰ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሰፉ ዉይይት ተደርጎበታል።