የ 06 ቀበሌ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኘው የምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ክትትል ላይ ላሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይሆን ዘንድ የ 06 ቀበሌ የተለያዩ የእርድ ከብቶች ፣ የምግብ ግብአቶች እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን ድጋፍ አድርገዋል ።
    በዚሁም የድጋፍ ስነ-ስርአት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ሱልጣን አልዬ በተለይም አስፈላጊና መሰረታዊ የሚባሉ እቃዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የ 06 ቀበሌ ወደ 300 ሺህ ብር የሚገመት ድጋፍ በማድረጋቸው አመስግነው ሌሎች ቀበሌዎችም መሰረታዊ የሆኑ አቅርቦቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ድጋፋቸውን አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባም ነው አቶ ሱልጣን አልዬ በእለቱ የተናገሩት ።
    ሀገራችን ኢትዮጲያ አሁን ላይ በርካታ ድሎችን እያስመዘገበች ባለችበት ወቅት እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር ጉዳት ለደረሰባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት አስተዳደሩ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተናግረው ይህንንም ድጋፍ ተከትሎም የ 06 ቀበሌ በተለይም የቀበሌውን ነዋሪዎች በማስተባበር ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆኑ የተለያዩ የእርድ ከብት ፣ የምግብ ግብአቶች እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን ድጋፍ በማድረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ አቶ አብዱሰላም ተናግረዋል ።
    የ 06 ቀበሌ ላደረጉት ድጋፍ የምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል ምክትል አዛዥ የሆኑት ኮረኔል ጌትነት አየነው አመስግነው የድሬዳዋ አስተዳደር እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም የተለያዩ ድጋፎች ማድረጋቸውን ተናግረው ከዚህ ቀደምም ለተደረገው ድጋፍ እንዲሁም አሁን ላይ ለሰራዊት እያደረጉት ላለው ድጋፍም ኮረኔል ጌትነት አየነው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።