ለረጅም አመታት ኑሯቸውን በውጭ አገር ያደረጉ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወንድምና እህቶች፤ ከናፈቁት የእናታቸው ማዕድ ለመቋደስ፤ የዘመናት እንባዋንም ለማበስ ወደ ትውልድ ከተማቸው ድሬዳዋ መግባት ቀጥለዋል።
የእናታቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት የገቡትና በድሬዳዋ ተወላጅ የሆኑት ወገን ወሰን፣ አደላሽ ክፍሌ፣ እና ስንታየሁ አርጋው፤ ዛሬ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በከንቲባው ጽ/ቤት የዳያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አቤል አሸብር እንግዶቹን በተቀበሉበት ስነ-ስርዓት ላይ፤ በድሬዳዋ የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ ታዳጊ እግር ኳስ ቡድኖች ተጫዋችና አሰልጣኞቻቸው ተገኝተው፤ የእንኳን ደህና መጣችሁ…


