በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም፤ በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበውና ከሀገር መልካም ገፅታ ግንባታና፣ ከቱሪዝም እድገት አንፃር ጉልህ ሚና የሚጫወተው ኃይማኖታዊው የጥምቀት በዓል፤ በአገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ላይ የተቃጣውን ጦርነት በህብረት መክተን፤ የልዩነት በሮችን በመዝጋት ለቀጣይ አገራዊ አንድነታችን ዝግጁ በሆንበት ወቅት የሚከበር ልዩ በዓል ነው።
በአስተዳደራችን የምትገኙ የእምነቱ ተከታይ የሆናችሁ የበዓሉ ተሳታፊ ወገኖቼ በሙሉ፤ የድሬዳዋችን መታወቂያ የሆነውን የሰላም እና የአንድነትን መልካም እሴት ይበልጥ በማጎልበትና፤ የኮሮና ቫይረስ በሽታ መከላከያ የጥንቃቄ መመሪያዎችን በመተግበር ራሳችሁን እየጠበቃችሁ፤ በዓሉን እንድታከብሩ ጥሪዬን እያቀረብኩ፤ በድጋሚ መልካም የጥምቀት ከተራ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ
የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
ጥር 10/2014 ዓም
ድሬዳዋ፣


