በአሰተዳደራችን በነገዉ ዕለት ”ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች ” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደዉ አገር አቀፍ የፓናል ውይይትና ፎቶ አዉደ ርዕይ ላይ ከ ሚሳተፉ የክቡር እንግዶች መካከል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚንስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ድሬ ዳዋ ገብተዋል ። የአሰተዳደሩ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የድሬዳዋ ብልጽግና ጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ከሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሰራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ደማቅ አቀባበል አድርገዉለታል። በ 11 ከተሞች ስለ ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል የሚካሄደዉ የፓናል ውይይትና የፎቶ ኤግዚቢሽን የመጀመሪያው መረሃ ግብር በጅጅጋ ከተማ የተካሄደ ሲሆን ሁለተኛዉ መድረክ በነገዉ ዕለት በከተማችን ” ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች ” በሚል መሪ ሃሳብ በልዩ ድምቀት የሚካሄድ ይሆናል።