አዲስ ፖለቲካዊ እይታ – አዲስ ሀገራዊ እምርታ ስልጠና በድሬዳዋ…

    የብልጽግና ፓርቲ ባደረጋቸው የመጀመሪያ ጉባኤ ካሳለፋቸው ቀጣይ አቅጣጫዎች መካከል ሀሳብን ወደ ተግባር መቀየር የሚችሉ ቁርጠኛ አመራሮችን መፍጠር ይገባል የሚሉ አንዱ ሲሆን ለዚህም የሚያግዝ እና የአመራሩን አቅም ሊያሳድግ የሚገባ የሚዲያ እና የተግባቦት ስልጠና ሦስት ተከታታይ ቀናት አስቆጥሯል በዛሬው እለትም ለፓርቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እየተሰጠ ይገኛል፡፡
    አዲስ ፖለቲካዊ እይታ አዲስ- አገራዊ እምርታ በሚል መሪ ቃል ለድሬዳዋ አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይም ተገኝተው ስልጠና የሰጡት የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና ለውጤታማ የህዝብ ግንኙነትና የተግባቦት ስራዎች ወሳኝ ናቸው ያሉት ሀላፊው በዘመናዊ የኮሚኒኬሽን ስርአት ውስጥ በክህሎት፣ በእውቀትና በቴክኖሎጂ አጠቃቀሙ የዳበረና ብቁ አመራር በመገንባት ህዝብን እና መንግስትን ይበልጥ በማቀራረብ በጋራ ለመስራት የሚያስችል አዲስ የፖለቲካ ማሳያ እምርታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
    አክለውም አስተዳደሩን የሚመጥን አቅም ያለው አመራር ለመገንባት ውጤታማ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ተቀራረበ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማምጣት ያመች ዘንድ በወቅታዊና አስፈላጊ አጀንዳዎች ላይ ስልጠና በመስጠት ለላቀ ውጤት መትጋት እንደሚገባ አስረድተዋል ፡፡
    በመድረኩ የኮሚኒኬሽን ዋና ዋና ግቦች ስልቶች፣ አቅጣጫዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሚሉ ሀሳቦች በስልጠናው በስፋት ተብራርተዋል፡፡
    ሀገርን ለማሻገር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ የተግባቦት ስራ እንደሚያስፈልግ የገለጽት የብልጽግና ፓርቲ ጥናት ምርምር ናሱፐርቪዥን ዘርፍ ሀላፊ እና የስልጠና መድረኩ አስተባበሪ አቶ ገዛህኝ ታዲዎስ የሃሠተኛ መረጃ መበራከት አሉታዊ ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ አመራሩ የሚዲያ እና የኮሙኑኬሽን ስራዎችን በማጠናከር ትክክለኝ መረጃን በፍጥነት ለህብረተሰቡ በመስጠት ሃገራዊ ለውጡን መደገፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
    የስልጠናው ተሳታፊ አመራሮችም ስልጠናው መሰረታዊ የሆኑ የተግባቦት ስልቶችን ከማስገንዘብ ጀምሮ መረጃ በተገቢው እና በአፋጣኝ በመመለስ ለህበረተሰቡ ማድረስ እንደሚገባ ሰፊ ግንዛቤ ከስልጠናው እንዳገኙ ተናግረዋል፡፡