“ስለ ኢትዮጵያ ” በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያን አሸናፊነት እና ከፍታን የሚያመላክት ነው የተባለ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት ዛሬ በድሬደዋ በደማቅ ሁኔታ ተካሄዱዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከጅግጅጋ ቀጥሎ ድሬደዋ ላይ ዛሬ ያዘጋጀውን ይህን የፎቶ አውደ ርዕይ የከፈቱት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ናቸው።
የፎቶ አወደ ርዕዩ ከ1960 ዎቹ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ ተስፋ እስከጣለችበት የሪፎርም ለውጥ ማግስት ያለውን ሁለንተናዊ ገፅታ እና ለህልውናዋ መረጋገጥ ያካሄደችውን የህልውና ዘመቻ የሚያሳይ ነው።
“ኢትዮጵያ አያሸነፈች ትሻገራለች” በሚል መሪ ሀሳብ ከተዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕዩ በተጨማሪ “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ ሃሳብ በመላው አገሪቱ የተጀመረው የኢንዱስትሪ ንቅናቄ ያመጣቸው ውጤቶች፤በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያሉ ማነቆዎች ዙራያ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርገዉ
ባቸዋል።
በዚህ የፎቶ አውደ ርእይ እና ፓናል ዉይይት ላይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ የክልል ም/ር/መስተዳድሮች ፣ባለሀብቶች ፣የአገር ሽማግሌዎች ፣የሃይማኖት አባቶች፣አባገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች ተሳታፊ ሆነዋል።


