ክቡር ሚንስትሩና ከንቲባችን የተሳተፉበት የከተማ ጽዳት ዘመቻ

    ክቡር ሚንስትሩና ከንቲባችን የተሳተፉበት የከተማ ጽዳት ዘመቻ በአሰተዳደራችን ዛሬ ጠዋት ተካናዉኑዋል።
    የፅዳት ዘመቻዉን ያዘጋጁት የድሬዳዋ የሌሊት ታክሲ ማህበር አባላት ናቸዉ ።
    በመርሀግብሩ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚንስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ፤ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመራሮች እና አባላት እንደሁም የሌሊት ታክሲ ማህበር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
    በዚሁ መርሀግብር ላይ የፅዳት ዘመቻ እንዲሁም የደም ልገሳ መርሀግብር የተካሄደ ሲሆን መሰል በጎ ተግባራት በሌሎችም የድሬደዋ አካባቢዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ክቡር ከንቲባ ከድር ለድሬ ትራንስፖርትየዝግጅት ክፍል ገልፀዋል፡፡
    የማህበሩ አባላት በበኩላቸው የማህበረሰቡን የትራንስፖርት ፍላጎት ከሟሟላት ባለፈ በመሰል በጎ ተግባራት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
    በስራቸው ላይ ሁሌም ትብብራቸውን ለሚያሳዩት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት እንዲሁም ለድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅ/መምሪያ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበዉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኮሙኒኬሽን ነዉ