የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር 03፣ 04፣ 05 አና 08 ቀበሌዎችን ምልከታ በማካሄድ የ2014 የመስክ ምልከታ መርሐ ግብሩን አጠናቀቀ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአሰተዳደሩ ከተማ ቀበሌዎችና በገጠር ክላስተሮች የ2014 በጀት አመት የ3ኛ ሩብ አመት የመደበኛና የ60 ቀናት እቅድ አፈጻጸም ላይ ስያካሄድ የቆየዉን የመስክ ምልከታ መርሐ ግብር በዛሬዉ እለት አጠናቀዋል።
በዛሬው ማጠቃለያ ምልከታዉም የድሬዳዋ አስተዳደር 03፣ 04፣ 05 አና 08 ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች ላይ በመዘዋወር የጽ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች በስራ ገበታቸዉ ላይ በመገኘት በህግና ደንብ መሰረት ህብረተሰቡን እነዴት አያገለገሉ እንደሚገኙና ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እንዴት ተቀናጅተው እየሰሩ እነደሆነ ተመልክተዋል።
በተጨማሪም ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ ቅሬታ ለማፍታት በሁሉም የአስተዳደሩ ተቋመት ባሉት አምስት የስራ ቀናት ዉሰጥ ሰኞና ዕሮብ የባለ ጉዳይ ቀን ስለ ሆነ ስብሰባም ሆነ ለሌሎች ጉዳዮች እንዳይኖሩና ሁሉም አመራርና ሰራተኞች ባለ ጉዳዮችን እንዲያስተናግዱ በአስተዳደሩ ምክር ቤት በተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት እንዴት እየተሰራ ነዉ የሚለዉን በጉብኝቱ ተመልክተዋል።
በምልከታዉም በአራቱ ቀበሌ አስተዳደር ጸ/ቤት የባለ ጉዳዮች ቀን በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉንና ዛረሬም በሚታየዉ እንቅስቃሴ ጥሩ አፈጻጸም ላይ እነዳለዉ እንዲሁም አመራሮችና ሰራተኖች በየቦታዉ በመገኘት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ ይታያል።
ከሁሉም ቀበሌ አስተዳደር ጸ/ቤት ዉስጥ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ግብአቶች አለመሟላት፣ የባለሙያ እጥረት፣ ቢሮዎች ጠባብ ከመሆናቸዉ አንጸር ምቹ ሁኔታ አለመኖሩ የሚታዩ መሆኑንና ከአስተባባሪዎችም ሃሳቦች ተነስተዋል።
በመጨረሻም በምልከታዉ የሚታዩ መልካም ስራና አፈጻጸሞች፣ ከባለፈዉ ምለከታ በቋሚ ኮሚቴው የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በማካተት የተስተካከሉ ለዉጦች የምያበረታታ ስለሆነ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና እነደ ችግር የተነሱ ጥያቄዎች የቀጣይ በጀት አመት እቅድ ዉስጥ በመካተት ከሚመለከተው አካል ጋር በመወያየት መፈታት እነዳለባቸዉ ኢንዲሁም በየቀበሌ አስተዳደር ጸ/ቤት የሚገኙ ሁሉም ማስተባበሪያዎች ከሴክተር መስርያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት የህብረተሰቡ የምልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና ቅሬታዎችን ለመፍታትና ለተሻለ አፈጻጸም ተጠናክሮ መሰራት እንደሚያስፈልግ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኡመር ሀሰን አቅጣጫ በማስቀመጥ ቋሚ ኮሚቴዉ የ2014 በጀት አመት የ3ኛ ሩብ አመት መስክ ምልከታ መርሐ ግብራቸውን አጠናቀዋል።


