” ስለ ኢትዮጵያ ” የተሰኘው 2ተኛው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት በዛሬው ዕለት በአስተዳደራችን ተካሄደ

    በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀውና “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እንግዶችን የእንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ውይይቱን አስጀምረዋል።
    በመድረኩም የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ፣ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በአወያይነት መድረኩን መርተውታል።
    በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ በአገራዊ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያሉ ዕድሎች፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሀሳቦችን በተመለከተ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አቶ መላኩ አለበል ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል።
    የኢንዱስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በቀጣይ አመታት የአገሪቷ ጂዲፒ ከ17 በመቶ በላይ ድርሻ እንደሚኖረው አቶ መላኩ አለበል በጥናታዊ ፅሁፋቸው ላይ ተናግረዋል።
    አገሪቷ ያላትን ትልቅ የዘርፉን እምቅ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ይቻል ዘንድ በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተሞክሮዎችን በመቀመር በተያዘው አመት “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ መጀመሩን ከመድረኩ ገልፀዋል።
    አቶ መላኩ በዚህ ጥናታዊ ፅሁፋቸው ላይ ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብቶች እና መልካም አጋጣሚዋቿን ዘርዝረው አቅርበዋል።
    ቀጣዩን ፅሁፉ ያቀረቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ናቸው አቶ ከድር የኢንዱስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት እንዲሁም የአመራሩ ሚና ምንድነው የሚል ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል።
    ጥናታዊ ፅሁፋቸው ላይ የድሬዳዋ ታሪካዊ
    ዳራን፣ የድሬዳዋን የኢንቨስትመንት እምቅ ሀብት እና እድሎች አሏት እንዲሁም ከተማዋ ለጅቡቲ ወደብ ቅርብ በመሆኗ ለባለሃብቱ ተመራጭ ያደርጋታል ተብለዋል።
    የድሬዳዋ የኢንዱስትሪ ልማትና ኢንቨስትመንት የበለጠ ለማምጣት ሰላም ወሳኙን ድርሻ ይወስዳል ያሉት ከንቲባው ህዝቡም ለሰላሙ ዘብ የሚቆም መሆኑን አስረድተዋል።
    በመጨረሻም የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ የግል ባለሀብቶችን በመወከል ፅሁፍ አቅረበዋል።
    በፅሁፋቸው ላይ እንደገለፁት ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች የሚሰጠውን ያህል ለሀገር ውስጥ ላሉ ባለሀብቶች ትኩረት ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
    በፓናል ውይይቱም የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል ተሳታፊዋች ያላቸውን ጥያቄዋች እና አስተያየቶች በመቀበል ውይይት ተደርጎባቸው መድረኩ ተጠናቋል።
    ቀጣይ ” ስለ ኢትዮጵያ ” የተሰኘው 3ተኛው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እና የፓናል ውይይት በሀረሪ ብሄራ