543 ሄክታር የመስኖ መሬት በማልማት 2136 አባወራዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የአሰተዳደሩ ግ/ዉ/መ/ኢ/ቢሮ አሰታወቀ።
በአስተዳደራችን ባለፉት አምስት አመታት በግብርና እድገት ፕሮግራም ምዕራፍ 2 የተከናወኑ የአነስተኛ መስኖ ልማት ተቋማትን ግንባታ 543 ሄክታር የመስኖ መሬት በማልማት 2136 አባ ወራዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ነዉ የግብርና ውሃ መዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል እና የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኤልያስ አሊይ የገለጹት ። የግብርና እድገት ፕሮግራም ምዕራፍ ፪ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች…


