በአስተዳደራችን ባለፉት አምስት አመታት በግብርና እድገት ፕሮግራም ምዕራፍ 2 የተከናወኑ የአነስተኛ መስኖ ልማት ተቋማትን ግንባታ 543 ሄክታር የመስኖ መሬት በማልማት 2136 አባ ወራዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ነዉ የግብርና ውሃ መዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል እና የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኤልያስ አሊይ የገለጹት ።
የግብርና እድገት ፕሮግራም ምዕራፍ ፪ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በግብርናው ዘርፍ ፈጣን ልማት እንዲረጋገጥ ለማድረግ በልማቱ ዕንቅስቃሴ ሰፊው ህዝብ በንቃት እንዲሣተፍና በተሳተፈበት መጠንም ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል ፡፡
በዘርፉ ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ ምርጥ ልምዶች ወደ ሁሉም አካባቢዎችና አርሶ አደሮች ተግባራዊ እንዲደረግ የተቀመጠውን አቅጣጫ ቢሆን ስራ ላይ መዋል በመጀመሩ ባለፉት ዓመታት የሰብል ምርት ዕድገት ተመዝግቧል፡፡ በህዝብ ተሣትፎ ሰፋፊ የተፈጥሮ ሃብት ስራዎችን መስራት በመቻሉ የተራቆቱ አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ ከማስቻሉም ባሻገር ለመስኖ ልማት ስራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ያከናወናቸው ተግባራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እንደ ነበር የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኤልያስ አሊይ ገልጸዋል ።
በኘሮግራሙ በሚተገበርባቸው ሁለቱ ክላስተሮች ስር በሚገኙ የተለያዩ ገጠር ቀበሌዎች በተገነባው የአነስተኛ መስኖ አውታሮች ግንባታና ጥገና እንዲሁም አነስተኛ የቤተሰብ መስኖ ውሃ ጉድጓድ ግንባታ ስራዎች 543 ሄክታር በመስኖ ማልማት የሚያስችል እና 2136 አባ ወራዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ይችል እንደሆነ ሀላፊው ጨምረው ገልጸዋል ።
መረጃዉን ያደረሰን የቢሮዉ የኮ/ህ/ግንኙነት ክፍል ነዉ


