“ምድር ባቡር ያለው ይዞታና ቦታ ምንም አልተነካም”
አቶ አየለ ወልደዮሀንስየድሬደዋ ምድር ባቡር ድርጅት ኃላፊ
ትውልድናእድገታቸውአዲስ አበባ ነው፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን የተማሩት አዲስ አበባ ተግባረ ትምህርት ቤት ነው፡፡ አሁን ላይ ኮሌጅ ሆኗል ይላሉ፡፡ ከዛም ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ ማሽኒስት ሆነው ዲፕሎማን አገኙ፡፡ ከዛም እንደወጡ በወቅቱ ስራ ተፈልጎ አልነበረምና የሚገኘው ዲፕሎማቸውንይዘው ቀጥታ በወቅቱ በነበረው ዘመቻ መምሪያ የሚባል ምደባ ነበረና ወደዛ ሄዱ፡፡ በዛ ምደባ መሰረትም ትራንስፖርት መገናኛ ሚኒስተርተመደቡ፡፡ትራንስፖርት መገናኛ ሚኒስተር ሄደው እጣ ሲያነሱደግሞ ኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ደረሳቸውና ወደ ድሬደዋ መጡ፡፡ ይህም የሆነው በ1975 በእኛ አቆጣጠር ከእርባ አመት በፊት ማለት ነው፡፡
ድሬደዋ ከገቡ በኋላ በወቅቱ ኢትዮጲያ ውስጥ የነበሩት ሁለት ትምህርት ቤቶች ብቻ ነበሩ ማለትም ለቴክኒክና ሞያ ተማሪዎች፡፡ የመጀመሪያው ባህርዳር አሁን ዩኒቨርስቲ የሆነው ፖሊ ቴክኒክ ሲሆን ሌላው ደግሞ አዲስ አበባ ተግባረድ ብቻ ነበረ የነበረው ይላሉ፡፡ ከነዚህ ተቋም የሚመረቁ ተማሪዎችም ሁለት አመት ሰርቪስ መስጠት ግዴታቸው ስለነበረ እሳቸውም ወደ ድሬደዋ ከመጡ በኋላ ሁለት አመት ሰርቪስ ሰጥተው በዛው ስራ መስራት ጀመሩ፡፡ስራቸውንእየሰሩም አለማያ ዩኒቨርስቲ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪዬያቸውንአገኙ፡፡ ከዛም እራሳቸውንእያሻሻሉበየድርጅቱ ውስጥ በተለያየ ደረጃ እየሰሩና እያደጉመጡ፡፡ በዚህም የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ በመሆን፣ የወርክ ሸፕ ሀላፊ በመሆን ከዛደግሞ በአስተዳደር እና በሃለፊነት በድርጅት ውስጥ ለረጅም አመት አገልግለዋል አሁንም እያገለገሉ ነው፡፡
ኢትዮ ምድር ባቡር ድርጅት ለየት ያለ ነው ይላሉ፡፡ለዚህም አንዳኛው ምክንያታቸው አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቻኛ ምድር ባቡር ድርጅት ነበረ ይላሉ፡፡ ከጅቡቲ አንስቶ አዲስ አበባ ድረስ 781 ኪ.ሜ ነው ያለው በዚህውስጥ ደግሞ የምድር ባቡር ቴክኞሎጂ ራሱ ለየት ያለ ነውም ይላሉ፡፡ እሳቸው ደግሞ ከዚህ ድርጅት ጋር እስከአሁን ድረስ ኖረዋል፡፡ አሁን ደግሞ የሚኒስተሮች ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔና በአስተዳደሩ እንዲጠቃለል በተደረገው መሰረት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የዚህ የድሬደዋ ምድር ባቡር ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል የዛሬ የድሬ ጋዜጣ እንግዳዬአቶ አየለ ወልደ ዮሀንስ፡፡
ውድ አንባቢያን ከዛሬው እንግዳዬ ጋር የድሬደዋ መሰረት ስለሆነው ምድርባቡር ታሪክና አሁን ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ በሰፊው አውርተናል እናንተም እንድትከታተሉኝ እጋብዛለሁ መልካም ንባብ እንዲሆንላቹ ተመኘሁ፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- በቅድሚያእንግዳችንለመሆንፍቃደኛስለሆኑበድሬጋዜጣስምከልብአመሰግናለሁ!
አቶ አየለ፡- እኔምየድሬጋዜጣእንግዳእንድሆንእድሉንስለሰጣችሁኝከልብአመሰግናለሁ!
ድሬ ጋዜጣ፡- በቅድሚያ ከኃላፊነቶ እንጀምርና በቅርቡ ነው ኃላፊነት የተሰጦትና ምን ተሰሞት?
አቶ አየለ፡-ሁለት ስሜት ነው የነበረኝ፡፡ አንደኛው ስሜቴ ወደ ስራ አስኪያጅነት ያመረጡኝ የማኔጅመንት አባላቱ ናቸው አስራ ሁለት የማኔጅመነት አባላት አሉ፡፡ ከእነሱ መካከልም ዘጠኙ እኔን መርጠው ማቅረባቸው በሰራተኛው ዘንድም በሀላፊዎች ዘንድም አመኔታንማግኘት ማለት ትልቅ ደስታ አለው፡፡ ሁለተኛ መስተዳደሩ እራሱ ይህንን ተቀብሎ ውሳኔ ሰጥቶ ክቡር ከንቲባው እኔን መሾማቸው ደግሞ በራሱ ለእኔ ሁለተኛ ደስታ ነው፡፡ ይህን ድርጅት ካለበት ሁኔታ ወደ አንድ ቦታ ለማሻገር በሃላፊነት መቀበሌም ደግሞ ራሴን በደንብ አድርጌ ለዚህ ጉዳይ እንድሰራ ሚያደርገኝ ነው፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- በጣም ጥሩ የኃላፊነት ቦታው እንዴት ነው? እንደጠበቁት ነው ያገኙት በአጠቃላይ እንዴት እንደሆነ ቢነግሩኝ?
አቶ አየለ፡- በእርግጥ ለስራው አዲስ አይደለሁም ምክንያቱም ድርጅቱ ተዳክሞ ምንም አይነት አጋዥ በሌለበት ጊዜ በራሳችን ጥረት ማለትም ድርጅቱ በራሱ ጥረት በሚያገኘው ገቢ 298 ሰራተኞችን ያስተዳድር ነበረ፡፡ባቡራችን ከዚህ እስከ ደወሌ ደርሶ መልስ በሳምንት ሁለት ቀን እያካሄደ የሰራተኛ ቤተሰብ እያከምን፣ መኖሪያ እየሰጠን ነበረ የቆየነው ይሄ ነገ ጠዋት የሆነ ነገር ቢጓደል ምን ላይ እንወድቃለን ሚል ስጋትን ይዘን ነበረ ስንሰራ የነበረው፡፡
አሁን ደግሞ እፊታችን ብትንገዳገዱ እኛ ደግፈን እናቆማቹሀለን ባጀት ድጋፍ እንሰጣቹሀለን ይሄንን እቅዳችሁን ከእኛ ጋር ትሰራላችሁ ብሎ አጠገባችን የሚቆም ግዙፍ የመንግስት አካል ካለን የሚሰማን ስሜት ከበፊቱ የበለጠ ሳንጨነቅ የምንሰራበት ስሜት ነው የመሚሰማን፡፡ እና ምን አለ አንድ ሰው አንድ ቢዝነስ ሲጀምር ቢዝነሱን ባለው ብር ቢጀምርም ብከስር ይሄነገር አለኝ ብሎ የሚያስብ ከሆነ ቢዝነሱን ያሳከዋል ያለፍርሀት ማለት ነው፡፡ አጠገባችንየሚረዳን ግዙፍ አካል አለ አሁንም ድጋፍ እየሰጠን ነው፡፡ ስለዚህ ምንም የሚያሳቅቀን ነገር ሳይኖር ከበፊቱ የበለጠ በድፍረት ሰራተኛውም ማኔጅመንቱም ይሰራል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በአጠቃላይ የኃላፊነቱን ቦታ በጣም ጥሩና አበርቺ ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- አሁን ላይ ከምድር ባቡር መጫወቻ ቦታ ጋር በተያያዘ ምንድነው የተፈጠረው?
አቶ አየለ፡- የድሬደዋ ምድር ባቡር እስፖርት ክለብ ጉዳይ በህግ የተያዘ ነው፡፡ ይስተካከላል የሚልእምነት አለኝ፡፡ ሰዎች መጫወቻ አያጡም ይህ ጉዳይ ረጅም ታሪክ አለው፡፡ረጅም ታሪክ አለውየምልበት ምክንያትም ምንድነው የምድር ባቡር ክለብ እንደ ኤሮፒያን አቆጣጠር በ1911 አ.ም ነውየተሰራው፡፡ የተሰራበትም ዋና አላማምሰራተኛውን፣ የሰራተኛውን ቤተሰብና የአካባቢውን ህብረተሰብ ለማዝናናት ነው፡፡ ማለትም በቦታው ላይ እንደ እግር ኳስ፣ ጅምናዚየም፣ ቡል በፈረንሳይ ባህል መሰረት፣ የሜዳ ቴኒስ፣ ባስኬት ቦል እና ሌሎችም የመሳሰሉትንጨዋታዎችእንዲጫወቱ ነው፡፡ እስካሁን ድረስም ህበረተሰቡንም ሰራተኛውንም እያገለገለ ነው ያለው፡፡ ከዚህ አገልግሎት ውጪም አይወጣም፡፡
ባለፈው በኢሀዲግ ዘመን ያቦታ የቴሌ ብረት ማከማቻ ይሁን ተብሎ ታስቦ ነበረ መመሪያም ተሰጥቶበት ነበረ፡፡ ያኔም እዚህ ያለን ማኔጅመንቶች በወቅቱም የማኔጅመንት ሀላፊም እኔ ነበርኩ እናም ያንን ውሳኔ አስቀርቼዋለሁ፡፡ ስለዚህ ዛሬም ሂደቱ ይስተካከላል፡፡ አሁንም ያለነው ለህዝቡ ነው ባለቤት የሆነውም ህብረተሰቡ ነው፡፡ ይሄ ህብረተሰብ የመስተዳደሩ አካል ነው መስተዳደሩ ይሄንን ያስብበታል፡፡ የሚለማበት መንገድንም ያስብበታል እናም ለግለሰብ ተሰጠ የሚባለው በፍርድ ያለሂደት ስለሆነ በፍርድ ይጠናቀቃል፡፡ ከዚህ በኋላ ህብረተሰቡ ብዙ ስጋት ያድርበታል ብዬም እኔ በበኩሌ አልጠብቅም፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- አሁን ቦታው ምን ላይ ነው ያለው?
አቶ አየለ፡- አሁን ቦታው በህግ ታግዶ ነው ያለው፡፡ ይህ ማለት ግን በከፊል ነው፡፡ የእግር ኳስ መጫወቻው ብቻ ነው እንጂ የማያገለግለው የተቀሩት ክፍሎች በሙሉ ያገለግላሉ፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- ቦታው እስከመቼ ነው ታጥሮ የሚቆየው?
አቶ አየለ፡- ታጥሮ የሚቆው ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ ነው፡፡ የህግ ጉዳይ አለ መስተዳደሩም ውሳኔ እስከሚሰጥበት ድረስ ነው፡፡ ነገር ግን ከህበረተሰቡ አገልግሎት ውጪ ይሆናል ብዬ አልተብቅም፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- ማነው ያሳገደው ካርታስያወጣው ማነው?
አቶ አየለ፡- የምድር ባቡር ድርጅት ነው ያሳገደው ካርታውን ደግሞ ያወጣው መሬት ማኔጅመንት ነው፡፡ አሁን ካሉት ካቢኔዎች ቀድመው የነበሩት ናቸው፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- ምን ለመስራት አስበው ነው ካርታውን ያወጡት?
አቶ አየለ፡- እሱ ላኛ ግልፅ አልሆነልንም፡፡ ከህግ አኳያ አሁን ያለው ነገር ምንድነው ቦታው እራሱ ለግለሰብ መሰጠት የለበትም የሚል ነው፡፡ የምድር ባቡር አቋም ይህ ነው በዚህ አቋሙ ደግሞ አሁንም ይቀጥላል፡፡ በህግ ሂደት ውስጥ ነው ያለው አሳግደነዋል በከፊል ደግሞ ህብረተሰቡ ይጫወታል፡፡ እዚህ ቦታ ላይ ማልማትም አስፈላጊ ከሆነ መንግስት ያለማዋል፡፡ ግለሰብ በዚህ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት የለበትም የሚል አቋም ነው እኛ ያለን ፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- እሺ ሲለማ በምን መልኩ ነው ለማልማት ያሰባችሁት?
አቶ አየለ፡- ገና ነው እቅድ አላወጣንበትም፡፡ መጀመሪያየህግ ሂደቱ ይለቅና ካለቀ በኋላ ህብረተሰቡ በሚፈልገው ፍላጎት መሰረት ነው የምንሄደው፡፡ ምክንያቱም ምድር ባቡር የቆየው ለህብረተሰቡ ብሎ ነው፡፡ አሁንም መስራት ያለበት ለህብረተሰቡ ነው፡፡ ስለዚህ ከህብረተሰቡ ጋር እንነጋገራለን በምን መልክ መሄድ አለበት የሚለውን እንወያያለን በመጀመሪያ ግን የህግ ሂደቱ ማለቅ አለበት፡፡
ስለሆነም አሁን ላይ ያለውና እኔ በትክክል የማውቀው ነገር ካርታው የተሰጠው ሰው ቦታውን አለማለሁ ብሎ መጣ አግባብ አደለም አልን ህግና ስርአት በተከተለ መንገድ ለፍርድ ቤት አቀረብን ፍርድ ቤቱ እግድ አወጣስለዚህ አሁን ታግዶ ቆሞ የህግ ሂደቱን እየጠበቀ ነው፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- እሺ አሁን ደግሞ ወደ ስራቹ ልምጣና አሁን ላይ በእናንተ በኩል ያላቹ የስራ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?
አቶ አየለ፡- መጀመሪያ ኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ነበርን፡፡ አሁን ግን ከመጋቢት 24 ወደዚህ ጀምሮ የድሬደዋ ምድር ባቡር ድርጅት ነው የምንባለው፡፡ እየሰራን ያለነው በትራንስፖርት እንቅስቃሴ በኩል ያለውን ነገር ነው አጠናክረን እየቀጠልን ያለነው፡፡ ከዚህ እሰከ ኪሊሌ 233 ኪ.ሜ የባቡር ትራንስፖርት በሳምንት ሁለት ቀን እንሰጣለን፡፡ ይሄ ደግሞ ዝቅተኛውንም ህብረተሰብ ያቀፈ ነው፡፡ በዚሁም አገልግሎት የምንሰጠው ማክሰኞና ቅዳሜ ቀን ነው፡፡ ሁለተኛ በወርክ ሾፓችን ግዙፍ ዎርክ ሾፕ አለን ምክንያቱም ለዘመናት የቆየ ነውና፡፡ በርካታ ማሽኖች አሉን አሁን ላይ በነዚህ ማሽኖች ድሬደዋም ይሁን አዲስ አባባ ከተማ ላይ ሊሰሩ ያልቻሉ ስራዎችን እየሰራን ነው፡፡
አሁን እራሱ በዚህ ሳምንት ውስጥ ኒው የሚባል ሸኒኔ ላይ የሚቋቋም የሳሙና ፋብሪካ ብረት መጠቅላል አቅቶት ብዙ ቦታ ሄዶ ነበረ እኛ ጋር መጥቶ አሁን እየሰራንለት ነው፡፡ ስለዚህ ለአንድ ፋብሪካ የሚሆን ብረት የመጠቅላል ስራ እየሰራን ነው፡፡ ሌሎችም አስቸጋሪ የሆኑ ነገሮች ማለትም የቴክኒክ ላይ ሌሎች ገራጆች ሊፈቱት ያልቻሉትን ነገር በዚህ በምስራቅ በኩል ያለውን ነገር መጥተው እኛ ጋር እየፈቱ ነው ያለው፡፡ ያለፈው ሳምንት ውስጥ እራሱ የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ብልሽት ገጥሞት የቆመበትንእስካባተር ሰርተን እኛም እነሱም እተጠቀምን ነው፡፡ ባጠቃላይ ቴክኒክ ክፍሉ እየሰራ ነው ያለው፡፡ ይሄንንም ደግሞ ማሳደግ የምንችልበት ሁኔታ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡ እራሱ ሎኮሞቲቭ ባቡራችንን እያደስን እያጓጓዝን ነው ያለነው፡፡ ሌላው ቱሪዝምንም እያስፋፋን ነው፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- ወደ ታሪካችን እንምጣና ድሬደዋ ከምድር ባቡር ጋር ያላት ቁርኝት ምን ይመስላል?
አቶ አየለ፡- በ1890 ዓ.ም ነው ከጅቡቲ ሀዲድ መዘርጋት የተጀመረው ከ 5 አመት በኋላ በ1895 ድሬደዋ ገባ፡፡ ድሬደዋ ከምድር ባቡር ምስረታ ጋራ የተያያዘ ታሪክ ነው ያላት፡፡ በወቅቱ የድሬደዋ ሙሉከተማበተለይም በደንብ የሚታወቁት መጋላና ከዚራ ናቸውበምድር ባቡራችን ነበረውሃ የሚያገኑት፡፡ ማለትም ለከተማው ሙሉ በሙሉ ውሃ በመስጠት፣ መብራት በመስጠት፣ አካባቢውን በማጽዳት አሁን ላይ ሻማቾች ማህበር የሚባለውን የመጀመሪያውን ኢኮንዋ የሚባለውን የጀመረው ምድር ባቡር ነበረ፡፡ ከፈረንሳይ የሚመጡ እቃዎችንም ለሰራተኛውና ለአካባቢው ሰው በቀላል ዋጋ በመሸጥ ህብረተሰቡን ያስተዳድርም ነበረ፡፡
ከ1926 ዓ.ም ወዲህ ግን መዘጋጃ ቤት ሲቋቋም ከተማዋን አስረክቦ የራሱን ይዞታና ቦታ ይዞ እስካሁን ድረስ የቆየ ነው ከመቶ ሀያ አመት በላይ፡፡ ስለዚህ ድሬደዋ ማለት ምድር ባቡር ማለት ነው፡፡ ማንኛውም የድሬደዋ ሰው ከምድር ባቡር ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ግንኙነት አለው፡፡ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ምድር ባቡር አለ፡፡ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያትነት አንድ ቀላል ነገር ላንሳ ፍሪጅ በማይታወቅበት ዘመን ቀዝቃዛ ውሃ በቀላሉ በማይገኝበት ጊዜ እኛ በረዶ አምርተን አንድ ሜትር የሚሆን ትልቅ ማምረቻ ነበረንናበነገራችን ላይ አሁንም አለን እና ሰዎች ቦኖ ይዘው መጥተው በረዶ እየቆራረጡ እየወሰዱ ቀዝቃዛ ውሃ እቤታቸው ይጠጡ ነበረ፡፡ ስለዚህ ምድር ባቡር ለጀመሪያ ጊዜ የድሬደዋን ህዝብ ቀዝቃዛ ውሃ ያጠጣ ነው፡፡
ይሄንን ያላደረገ የድሬደዋ ነዋሪ ደግሞ የለም ማለት አይቻልም፡፡ ምድር ባቡር ገብቶ ሰርቶ ያሎጣም ሰው የለም፡፡ መስራቱ ብቻም አደለም በምድር ባቡር ሄዶ ህይወቱን ያለወጠ ሰው የለም፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አደጋው ሲደርስም እጁ የተቆረተ ሰው አለ፡፡ ስለዚህ የድሬደዋ ህዝብ ልብ ውስጥ ምድር ባቡር አለ፡፡ሌላው ቢቀር በአሁኑ ሰዓት ሰዓት ሲጮህ ይሰማል፡፡ በዚህም ሁሉም የድሬደዋ ነዋሪ ጅቦጮኸ ይላል፡፡ ይህ ማለት ሁሉም ሰው የእለት ፕሮግራሙን የሚያከናነው በድርጅቱ ሰዓት መጮህ ነው ተማሪውም ሰራተኛውም፡፡ ተሳስተን አንድ ቀን ሰዓት ባናጮህ ሰዎች ምን ሆናቹ ነው ብለው ይመጣሉ፡፡ እና ይሄን ያህል ታሪካዊ ይዘት አለው፡፡
ወርክሾፖቻችን በ 1901 ዓ.ም የተሰሩ ናቸው፡፡ ግን እስከ ዛሬ አዲስ ናቸው፡፡ አፍሪካ ውስጥ የሌለ እኛ ጋር ያለ ተሸከርካሪ ድልድይ ምርጥ ወርክሾፖች እኛ ጋር አሉ፡፡ ሎኮሞቲቮችን እናስተካክላለን በሳምንት አንድቀን የባቡር ሽርሽር የሚመጣ ሰው ካለ አዘጋጅተን ሽኒሌ አድርሰን እንመልሳቸዋለን፡፡ ይሄ ደግሞ ለከተማዋ አሁንም ላይ ማህበራዊ አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ ወደፊትም እንሰጣለን፡፡ ምድር ባቡር ከድሬደዋ ህዝብ ማህበራዊ ህይወጥ ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ወደ 257 ቤቶችን እናስተዳድራለን፡፡ አብዛኛው ያለው ጡረተኛና የጡረተኛ ቤተሰብ ነው፡፡ አብዛኛው መስሪያ ቤቶች ጋር ብንሄድ መጥተው ልምድ የሚወስዱት ከእኛ ጋር ነው፡፡
አዲሱ ምድር ባቡር ሲቋቋም እኛ ጋር መጥቶ ነው ልምዱን ወስዶ የሄደው፡፡ አሊያንስ ኢትዮ ፍራንስ ምድር ባቡርን ተከትሎ የተቋቋመ ነው፡፡ እነዚህ የካቶሊክ፣የሚካኤል ቤተክርስቲያንና የግሪክ ቤተክርስቲያን የምድር ባቡርንምስረታ ተከትለው የተሰሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለዚህ ሁሉ ነገር መሰረቱ የድሬደዋ ምድር ባቡር ነው፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- አሁን ላይ ታዲያ በፊት የነበረው የምድር ባቡር ሁኔታ አለ የቀስሞ ዝናው እያደገ ነው የመጣው ወይስ እየጠፋ ያለውን ነገር ቢነግሩኝ?
አቶ አየለ፡- እርግጥ ነው ወርዷል፡፡ በ1890 ዓ.ም ከጅቡቲ ተነስቶ በ 1909 ዓ.ም አዲስ አበባ ደርሷል፡፡ አዲስ አበባ ሲደርስና ስራ ሲጀምር 54 ጎታቾች ናቸው በወርድ ስራ የጀመሩት፡፡ 781 ኪሎ ሜትርም ይሰራ ነበረ፡፡ በወቅቱ ሃዲዳችን አንድ ሜትር ስፋት ነው ያለው አሁን እስታንዳርዱ አንድሜትር ከ 56 አካባቢ ነው፡፡ እናም በወቅቱ አንድ ሜትር ስፋት ያለው ባቡር በአፍሪካ ውስጥ ዘመናዊ ነበረ፡፡ እናም በጣም ዘመናዊ ባቡር ነበረ አፄ ሚኒሊክ ያስገቡት፡፡ ቴክኖሎጂው ግን ቆሞ አልጠበቀንም እና ቴክኖሎጂ ሲበር እና እዛው ተገኘን እና በዚህ ምክንያት የቀድሞው ዝናችን ቀነስ ብሏል፡፡ ሌላው ደግሞ ሰው ሰራሽም ተፈጥሮም ጎድቶናል ያንን ደግሞ መተካት አልቻልንም ፡፡
ሰው ሰራሽ የምንለው ጦርነት ሲሆን የሆነ ችግር ሲፈጠር መጀመሪያ ተጠቂ የሚሆነው የኛ ትራንስፖርት ነው፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጲያና በሶማሌ ጦርነት ጊዜ ወደ 20 የሚጠጉ ድልድዮች ናቸው በፈንጂ የፈረሱብን መልሶ ተገንብቶ ቢሰራም፡፡ ከዛ በኋላምየተነሱ ችግሮች ደግሞ ባቡራችን በፈንጂ ተመቷል ሰዎች ሞተዋል ሰራተኞቻችን ሞተዋል በርካታ ህይወትም አልፎበታል፡፡ የተቃጠለ ጋሪ አለ እና በርካታ ነገር ማንሳት ይቻላል፡፡ ይህን እንደ ሰው ሰራሽ ችግር ብናነሳ የተፈትሮ አደጋ ደግሞ ጎርፍ አለ፡፡ በየወቅቱ በአየር ለውጥ ምክንያት ጎርፎች እየጨመሩ መጥተዋል፡፡ እኛ አነስተኛ ነው ብለን ምናስበበት ቦታ ላይ ከፍተኛ ጎርፍ መጥቶ ድልድዮችን እየሰበረ ሃዲዶችንም እየሰበረ ነው ያለው፡፡
በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ የራሱ የማኔጅመንት ችግር ነበረው፡፡በነበረው የማኔጅመንት ችግር ላይ የነበረው ምንድነው የሁለት ሀገር ስምምነት ስለነበረ የነበረው ስራ ሳይሆን የፖለቲካል ስምምነት ነበረ፡፡ ይህ ደግሞ በወቅቱ መሻሻል ይገባው የነበረውን የማኔጅመንት ችግር አላሻሻለውም፡፡ ሎኮሞቲቮች መጨመር ሲገባቸው አልተጨመሩም ሁል ጊዜ እርዳታ ጥየቃ ነው እራሱን በራሱ መሄድ አልቻለም፡፡ ይሄ ደግሞ ምን አድርጎታል ከ781 ኪሎ ሜትር ዛሬ ወርዶ በ203 ኪሎ ሜትር ብቻ እንዲሰራ አድርጎታል፡፡ እና ይሄን ያህል ወርደናል፡፡
ሌላው ደግሞ በጣም ያስቸገረን ነገር የኢሮፓ ገበያ ወደ ሀምሳ ሚሊየን ይሮ ድጋፍ ሰጥቶን ነበረ፡፡ኢውሮፒያኖች ድጋፍ ሲሰጡ የራሳቸው የሆነ የሚያስቀምጡት መስፈርት አለ፡፡ ከዛም ከኢሮፓ ኮንስታ ጁንቲ ሜምበር የተባለው ድርጅት 100 ኪ.ሜ በጣም ያረጀውን ሀዲድ ለውጥ ተብሎ መጣ፡፡ 50 ይሮ ይዞ መጣ በ3 አመት ለውጥ ተብሎ ውል ገባ ግን ደግሞ በ6 አመት እንኳን 100 ኪ.ሜ 20 ኪ.ሜ እንኳን በስርአቱ ሳይጨርስ ነው የወጣው፡፡ ይሄ የበለጠ ድርጅቱን አዳከመው፡፡
ከዛ በኋላ በሰራተኛውና በአካባቢው ባሉ ሰዎች ጥረት ከዚህ እስከ ጅቡቲ መስመር መሰራት ተጀመረ፡፡ ወደ ላይ የመትሀራ ወንዝ መሙላት የተፈጥሮ ችግር ስለሆነ ሀዲዱን ውጦታል፡፡ እዚህ ኪሎ ሜትር 4 ላይ በጎርፍ ምክንያት ሃዲዱ ተመቶ እንዲሁም ትልቅ ድልድይ በጎርፍ ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል፡፡
ሌላው ደግሞ አዲሱ ሀዲድመስመር ሲዘረጋ አብዛኛው በእኛ መስመር ላይ ነበረ ያለፈው የሄ ደግሞ የኛን የባቡር እንቅስቃሴ አቆመው፡፡ ከዚህ እስከ ጅቡቲ ሲሄድና ጅቡቲ ሲገባ አንድ ቦታ ላይ ኦቨር ላፕ አድርጎ ቆመ፡፡ በዚህም የአዲስ አበባ ምድር ባቡር የጅቡቲ ምድር ባቡር ስራዎችን ሁሉ አቀሙ፡፡ የድሬደዋ ምድር ባቡር ብቻ ከድሬደዋ እስከ ደወሌ 203 ኪ.ሜ እንቅስቃሴውን አጥብቆ ያዘው፡፡
ይህንን ደግሞ እንደገና አጥብቆ ለማስቀጠል ሚኒስተሮች ምክር ቤት ውሳኔ በወሰነው መሰረት በድሬደዋ መስተዳደር ስር ገባ፡፡ የድሬደዋ መስተዳደር ደግሞ የነበረውን ዝናውን ለመተበቅ ከሜኤሶ ጀምሮ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ከታች በኩል ያለውን ደግሞ እስከ ጅቡቲ ለማድረስ የራሱ የሆነ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ከጀመርንም አንድ ሳምንታችን ነው፡፡ በዚህም ትልቅ ተስፋ አለን፡፡ ግድም ደግሞ የምንታገልበት ምክንያቱ ድሬደዋ አለች ለመባል ምድር ባቡር መኖር አለበት፡፡ ማንም ሰው ሲመጣ መጀመሪያ የሚያየው ሼማንደፍርን ነው፡፡ ሼማንደፍር በድሬደዋ መሰረት ስለሆነ ክብርና ሞገሱን ይዞ እንዲቀጥል እኛም መስተዳደሩም ጥረት ማድረግ አለብን ያንን እያደረግንም ነው፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- በመጨረሻ መናገር የሚፈልጉት ነገር ካለ?
አቶ አየለ፡- አንደኛው ህብረተሰቡ በደንብ ማወቅ ያለበት ምድር ባቡር ያለው ይዞታና ቦታ ምንም አልተነካም፡፡ እኔ አሁን የማቀው ነገር ምድር ባቡር የያዛቸውን ቤቶችና ቦታዎችን አስከብሮ እየቀጠለ ነው፡፡ በድርጅቱ ውስጥ ያለው መዋቅር ምንም አልተነካም ሌላው ቢቀር ድርጅቱን የሚመራው አካል እነሱ ሳይሆኑ የሰየሙት ማኔጅመንቱ ራሱ ነው የመረጠው፡፡ አንድም ጣልቃ የገባብን አካል የለም፡፡ እኛደግሞ ትልቅ ደስታ ያገኘንበት ነገር ምንድነው ከዚህ በፊት ለኢትዮ ጅቡቲ የተቋቋመው ቦርድ ለአስራ አንድ አመት ተሰብስቦ አያውቅም አሁን ያለው አካል ነው የሚሯሯጠው፡፡
የድሬደዋ መስተዳደር አሁን ላይ ቦርድ አቋቁሟል እና ቦርዱ በቅርበት አለን፡፡ የስራ ቦርድ ነው ላሉብን ችግሮችም መልስ እያገኛን ነው፡፡ ድሬደዋ የበረሃ አበል አላት ሁሉም መስሪያ ቤቶች የፌደራልም ሆኑ የመስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የበርሃ አበል አላቸው፡፡ የድሬደዋ ምድር ባቡር ግን ይሄን ጥያቄ አቅርቦም የበርሃ አበል አልተከፈለውም፡፡ አሁን ግን ይሄን ሰራተኛው በአንድ ስብሰባ ከንቲባውን ጠየቀ ተፈቀደ እናም ከግንቦት አንድ ጀምሮ 20 ፐርሰንትየበረሃ አበል ይከፈላቸዋል፡፡ ስለሆነም ለብዙ አመት የተከለከለውን መስተዳደሩ እኔ በርሃ ነኝ እኔ ጋር የሚሰሩ ሰራተኞች የበርሃ አበል ማግኘት አለባቸው ብሎ ዛሬ ላይ ይከፈላል፡፡ ስለሆነም አሁን ላይ ተጨመረልን እንጂ የጎደለን የለም፡፡
ድሬ ጋዜጣ፡- አቶ አየለ በጣም ጥሩ ቆይታ አድፈርገናል ለዚህም በጣም አመሰግናለሁ!
አቶ አየለ፡- እኔም በጣም አመሰግናለሁ!
በኤደን ሳሙኤል


