ድሬዳዋ ልዩ ድጋፍና ትኩረት እንደሚያስፈልጋት ተገለጸ።

    የብልጽግና ፓርቲ ዋናው ጽ/ቤት የሱፐርቪዥን ቲም የመውጫ (Exit) በ90 ቀናት እቅድ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የክትትልና ድጋፍ ግብረመልስ ሰጥተዋል።
    በግብረመልስ መድረኩ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀርን ጨምሮ የፓርቲው አስተባባሪ ኮሚቴና የካቢኔ አባላት በተገኙበት በምልከታው የታዩ ጠንካራና ቀጣይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ተነስተዋል።
    በከተማና በገጠር የታዩ መልካም ነገሮች የአመራሩ ውጤት መሆኑን የገለጹት የሱፐርቪዥን ቲሙ በአስተዳደሩ የተሻለ አቅምና ተቀባይነት ያላቸው አመራሮች እንደምቹ ሁኔታ በመጠቀም ተመርቀው ያለ ስራ የተቀመጡ ለገጠር ስራ አጥ ወጣቶች ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል።
    አክለውም በ90 ቀናት እቅድ በቀሪ ቀናቶች ያልተጠናቀቁ ስራዎችን በማካተት በተቀናጀ አግባብ መከናወን ይገባል ብለዋል።
    በመጨረሻም ከታዩ ተቋማት በአብዛኛው ጠንካራ ጎኖች የሚበዛባቸው መሆኑን በተወሰነ ደረጃ ያልተሟሉ ጉዳዮችና ዘላቂ ያልሆኑ አገልግሎቶች ዘላቂ እንዲሆኑ በማንሳት በአጠቃላይ በምልከታው ደስተኛ መሆናቸውን በመጥቀስ የድሬዳዋ ቻርተር ማፀደቅን ጨምሮ ልዩ ድጋፍና ትኩረት የሚያስፈልጋት አስተዳደር መሆኗን ገልጸዋል::