በድሬደዋ አስተዳደር የሚገኙ አመራሮች በከተማዋ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን እና የምስራቅ አየር ምድብን ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡ ጉብኝቱ አመራሩ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በመመልከት ለቀጣይ የልማት ጉዞ በየተሰማራበት መስክ የድርሻውን እንዲወጣ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ተጠቁሟል፡፡

    ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንደሁም ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና አመራሮች በድሬደዋ ደረቅ ወደብ ሬዳዋ ሞተርስ ፤የምስራቅ አየርምድብ ፣የናሽናል ሰምንት ፋብሪካ እና የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
    ድሬደዋ አሁን ያላትን የልማት አቅም ሙሉ ለሙሉ በመጠቀም ለዜጎች በቂ የስራ እድልን በመፍጠር የተሻለ እና ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎች በከተማዋ እንዲበራከቱ በስራ ውስጥ ያሉትን ኢንዱስትሪዎች አቅም ማጎልበት እንደሚያስፈልግ ነው በጉብኝቱ የተጠቆመው፡፡ ክቡር ከንቲባ ከድር በተለይ አመራሩ የተጣለመትን ህዝባዊ አደራ ባግባቡ በመወጣጥ እን ወደ ከተማዋ ለሚመጡ ኢንዱስትሪዎች ምቹ እድልን በመፍጠር ከተማዋን ወደነበረችበት ቀደምትነቷ ለመመለስ እንዲንቀሳቀስ ነው መልእክት ያስተላለፉት፡፡
    ሌላው የምስራቁ ብሎም የሀገር የሰላም ዋስትና የሆነውን የምስራቅ አየር ምድብ እንደሁም በፈጣን የሪፎርም ሂደት ውስጥ ያለውን የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ቅጥር ጊቢ የተጎበኘ ሰሆን አመራሩ ከመሰል ተቋማት ልምዶችን በመቀር በየዘርፉ ውጤታማ ስራን እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል፡፡
    በ ዘዉገ አዉላቸዉ