ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 69ኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል።

    በስነ ስርዓቱም፣ ከበርካታ ዘርፎች ተውጣጥተው የጥቁር አንበሳ ኮርስ የተከታተሉት ምሩቃን የምክትል መቶ አለቅነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምሩቃኑ ነገ በሚደርሱበት የኃላፊነት ልክ፣ ሀገርን ለመምራት እንዲቻላቸው ዘወትር እንዲተጉ አሳስበዋል። በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መሰተዳድሮችና ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል ።

    Read More

      የአካባቢያችንን ሰላምና ፀጥታ በመጠበቅ የተጀመረውን ለውጥ አጠናክረን እናስቀጥላለን- የድሬዳዋ የሴቶች ሊግ አመራሮችና አባላት

      ግንቦት 21 ቀን 2014 የአገሪቱን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት የድርሻቸውን ኃላፊነት በቁርጠኝነት እንደሚወጡ የድሬዳዋ የሴቶች ሊግ አመራሮችና አባላት ገለፁ። “የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና ” በሚል መርህ በድሬዳዋ የብልፅግና ሴቶች ሊግ ጉባኤ እየተካሄደ ነው። በጉባኤው ላይ የተሳተፉት የድሬዳዋ ሴቶች ሊግ አመራሮች እና አባላት እንደተናገሩት ፤ ለውጡን ተከትሎ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እየጎለበት…

      Read More

        ለበርካታ ዓመታት ማነቆ የነበረውን የቀበሌ ቤት መስጠት ችግርን በመፍታት ለዜጎች ቤትን የመስጠት ተግባር በ ቀበሌ 05 አሰተዳደር

        በአስተዳደራችን በተቀመጠው የህዝቦችን ጥያቄ በአፋጣኝ የመፍታትና ምላሽ የመስጠት የ90 ቀናት ዕቅድ መሰረት በቀበሌ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት በፍል ውሃ ቀጠና ለበርካታ ዓመታት ማነቆ የነበረውን የቀበሌ ቤት መስጠት ችግርን በመፍታት ለዜጎች ቤትን የመስጠት ተግባርን በይፋ አስጀምረናል፡፡ በዛሬው ዕለት የአስተዳደሩ የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊና የቀበሌው ደጋፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በተገኙበት ቤትን ለደሃ የማስረከብ ተግባር ለተረኛዋ ወ/ሮ…

        Read More

          የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበርካታ አመታት የመልካም አስተዳደር ችግር የነበረውን የሀሎቡሳለገኦዳ ሚርጋ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ጎበኙ።

          በአስተዳደራችን ካሉ የገጠር ቀበሌዎች በሀሎ ቡሳ እና ለገኦዳ ሚርጋ ለበርካታ አመታት የመልካም አስተዳደር ችግር በሚል ሲነሳ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር እንዲሁም በውሃ እጦት ሲነሱ የነበሩ የውሃ ወለድ በሽታዎች ለመከላከል በሚል የተጀመረው የሀሎቡሳለገኦዳ ሚርጋ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት አቅም ላይ መድረሱን መመልከት ተችሏል። በጉብኝቱ ሂደት አንዳንድ የአከባቢው ነዎሪዎች እንደገለፁት ለበርካታ አመታት…

          Read More