ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 69ኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል።

    በስነ ስርዓቱም፣ ከበርካታ ዘርፎች ተውጣጥተው የጥቁር አንበሳ ኮርስ የተከታተሉት ምሩቃን የምክትል መቶ አለቅነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።
    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምሩቃኑ ነገ በሚደርሱበት የኃላፊነት ልክ፣ ሀገርን ለመምራት እንዲቻላቸው ዘወትር እንዲተጉ አሳስበዋል።
    በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መሰተዳድሮችና ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል ።