ለበርካታ ዓመታት ማነቆ የነበረውን የቀበሌ ቤት መስጠት ችግርን በመፍታት ለዜጎች ቤትን የመስጠት ተግባር በ ቀበሌ 05 አሰተዳደር

    በአስተዳደራችን በተቀመጠው የህዝቦችን ጥያቄ በአፋጣኝ የመፍታትና ምላሽ የመስጠት የ90 ቀናት ዕቅድ መሰረት በቀበሌ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት በፍል ውሃ ቀጠና ለበርካታ ዓመታት ማነቆ የነበረውን የቀበሌ ቤት መስጠት ችግርን በመፍታት ለዜጎች ቤትን የመስጠት ተግባርን በይፋ አስጀምረናል፡፡
    በዛሬው ዕለት የአስተዳደሩ የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊና የቀበሌው ደጋፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በተገኙበት ቤትን ለደሃ የማስረከብ ተግባር ለተረኛዋ ወ/ሮ አበራሽ መንግስቱ ተገቢውን የቤት አከራይ ኮሚቴ እና የካቤኔ ውሳኔ በማሳረፍ እንዲደርሳት ተደርጓል፡፡
    የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደተናገሩት ለዜጎች በችግራቸው መድረስ፤ ለመንግስት አሰራር ደግሞ በእውነትና በእውቀት መምራት በሚፈለግበት በዚህ ሰዓት ለወ/ሮ አበራሽ መንግስቱ በዛሬው ዕለት ቤቱን በመስጠታቸው መደሰታቸውን ገልጠው ይህ ተግባር በተቻለ መጠን በፍጥነት ቤቶችን እያዩ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ መስጠቱ ሊስፋፋ ይገባል ብለዋል፡፡ ከብልሹ አሰራርና ማነቆዎች በመውጣትም የህዝቦችን አሁናዊ ወሳኝ ጥያቄ በአገልግሎት አሰጣጡና በተለይም በነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥም ላይ ሊደገም ይገባል በማለት ገልጠዋል፡፡
    በመጨረሻም ቤት ላገኘችው ወ/ሮ አበራሽ መንግስቱ እንኳን ደስ ያለሽ በማለት ለተባባሪ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡